ለ፲ ቀናት በዝግ ሲካሔድ የቆየው የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዐተ ጉባኤ ዛሬ ከሰዓት በሚሰጠው መግለጫ እንደሚጠናቀቅ ተገለጸ።

ለ፲ ቀናት በዝግ ሲካሔድ የቆየው የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዐተ ጉባኤ ዛሬ ከሰዓት በሚሰጠው መግለጫ እንደሚጠናቀቅ ተገለጸ።
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ትውፊት መሠረት የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዐተ ጉባኤ በዓመት ሁለት ጊዜ በጥቅምት 12 እና በግንቦት ርክበ ካህናት (የትንሣኤ 25ኛ ቀን) ይካሔዳል።
በዚህ ዓመት የጥቀምት ቅዱስ ሲኖዶስ መልዐተ ጉባኤ ከጥቅምት 12/2017 ዓ/ም ጀምሮ ለተከታታይ 10 ቀናት ሲካሔድ የቆየ ሲሆን ዛሬ ጥቅምት 21/2017 ዓ/ም ከሰዓት በኋላ በሚሰጠው የጉባኤ መግለጫ እንደሚጠናቀቅ ተገልጿል።
የዚህ ዓመቱ ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዐተ ጉባኤ በ28 አጀንዳዎች ሲወያይ መቆየቱም ታውቋል።
የጉባኤውን የቀን ውሎና ውሳኔዎች በተመለከተም በመጋቤ ሃይማኖት አባ አብርሃም ገረመው የሰሜን አፍሪካ ሀገረ ስብከት ሥራ አእኪያጅና የቅዱስ ሲኖዶስ ምክትል ጸሐፊ አማካኝነት መረጃዎች ለተመልካች ሲደርሱ መቆየታቸው የሚታወስ ነው።

Source:-አበባ ሀገረ ስብከት ሚዲያ