የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ባሳለፍነው ዓመት ከ631 ሚሊዮን ብር በላይ ለመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት በማስገባቱ ከፍተኛ ተሸላሚ ሆነ።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፵፫ኛው የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ለጥቅምት ፬/፳፻፲፯ ዓ/ም ጀምሮ ሲካሄድ የቆየ ሲሆን በዛሬው ዕለት ተጠናቋል።
በማጠናቀቂያ መርሐ ግብሩ በየዘርፉ አህጉረ ስብከትን በማወዳዳር የእውቅናና ሽልማት መርሐ ግብር ተከናውናል።
ከማወዳዳሪያ ዘርፎቹ መካከል አንዱ ከፍተኛ አጽተዋጽኦ በማስገባት ዘርፍ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት 631 ሚሊዮን ብር በላይ ለመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ገቢ ያደረገ ሲሆን በዚህም 1ኛ ደረጃን በመውጣት ተሸላሚ ሆኗል።
የእውቅና ሽልማቱን ብፁዕ አቡነ ሄኖክ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስእና የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ሊቀ ማእምራን የማነ ዘመንፈስ ቅዱስ ከብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ እጅ ተቀብለዋል።
ከአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ቀጥሎም የሸገር ከተማ ሀገረ ስብከት ከ28 ሚሊዮን ብር በላይ እንዲሁም የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ከ26 ሚሊዮን ብር በማስገባታቸው ሁለተኛና ሦስተኛ ደረጃን ይዘው ተሸልመዋል።
የሀገረ ስብከቱ ለመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ያስገባው ገቢ ከ2015 ዓ/ም የአገሎግሎት ዘመን ገቢ አንጻር ሲታይ የ122 ሚሊዮን ብር ልዩነት በብልጫ ማሳየቱም ተገልጿል።
ለመንበረ ፓትርያርክ በፐርሰንት ገቢ የሚሆነው አስተዋጽኦ ለቤተ ክርስቲያን ሁሉን አቀፍ ሥራዎች፤ ለመደበኛ በጀት እንዲሁም በገቢ ራሳቸውን ላልቻሉ አህጉረ ስብከት የሚደለደል መሆኑም ለማወቅ ተችሏል።
የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ መሠረት ከሌሎች አህጉረ ስብከት በተለየ መልኩ ከገቢው 65 % ለመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት እንደሚያስገባ የሚታወስ ነው።

Source:-አበባ ሀገረ ስብከት ሚዲያ