የ፵፫ ኛው የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዓለም አቀፍ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ በዛሬው ዕለት ተጀምሯል።
የ፵፫ ኛው የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዓለም አቀፍ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ በዛሬው ዕለት ተጀምሯል።
ጉባኤ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ርእሰ መንበርነት እየተመራ ይገኛል።
ቅዱስነታቸው የመክፈቻ መልእክት አስተላልፈዋል።
ብፁዕ አቡነ አብርሃም የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክሆነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ፣ የባሕር ዳርና የሰሜን ጎጃም አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የዋና መሥሪያ ቤቱን አጠቃላይ ሪፖርት አሰምተዋል።
በሪፖርቱ የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ በዓመቱ ያከናወኗቸውን ሐዋርያዊ አገሎግሎቶች፣ የየመምሪያውና የድርጅቶች፣ የመንፈሳዊ ዩኒቨርሲቲና ኮሌጆች ዓመታዊ ሥራ ክንውኖችን አቅርበዋል።
በጉባኤዎ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ ብፁዕ አቡነ ሄኖክ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ የየመምሪያና የድርጅት ሐላፊዎች፣ ሊቀ ማእምራን የማነ ዘመንፈስ ቅዱስ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ ፣ የአህጉረ ስብከት ሥራ አስኪያጆች፣ የሀገረ ስብከቱ የዋና ዋና ክፍል ሐላፊዎች፣ የክፍለ ከተማ ሥራ አስኪያጆች፣ የገዳማትና የአድባራት አስተዳዳሪዎች፣ ምክትል ሊቃነ መናብርትና የተለያዩ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
ጉባኤው እስከ ጥቅምት ፲/፳፻፲፯ ዓ/ም እንደሚቆይ ከወጣው መርሐ ግብር ለማወቅ ተችሏል።
የመጀመሪያው የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዓለም አቀፍ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ በ1975 ዓ/ም እንደተካሔደ መረጃዎች ያመለክታሉ።
Source:-አበባ ሀገረ ስብከት ሚዲያ