የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ወይብላ ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን ላይ የተፈጸመውን አስነዋሪ ድርጊት እንደሚያወግዝ አስታወቀ!!!

የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ በጥምቀት በዓል ላይ በቡራዩ ከተማ አስተዳደር የተፈጸመውን ሕገወጥ ድርጊት በመቃወም መግለጫ አወጥቷል።

ጉባኤው በመግለጫው ሃይማኖቶች የትህትና፣ የሰላምና የአንድነት፣ የፍቅርና መከባበር መሠረቶች ናቸው ብሏል።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ለዘመናት የሰላም መሠረት ሆና ዘልቃለች ያለው የጉባኤው መግለጫ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ሃይማኖትን ሽፋን አድርገው ግጭት ለመፍጠር የሚንቀሳቀሱ ኃይሎችን አጥብቀን እንቃወማለን ነው ያለው።

ጥር 12 ቀን 2014 ዓ.ም በቡራዩ ከተማ አስተዳደር በሕግ ማስከበር ሽፋን በቤተ ክርስቲያኗ ላይ የተቃጣው ድርጊት ፍጹም ሕገ ወጥ ነው ያለው መግለጫው መንግሥት አጥፊዎችን ተከታትሎ ለሕግ እንዲያቀርብም ጠይቋል።

መንግሥት የሃይማኖትን እና የዜጎችን ሰላም እና ደኅንነት የማስጠበቅ ኃላፊነቱን እንዲወጣ የጠየቀው የጉባኤው መግለጫ የሕይወት፣ የአካል እና የመንፈስ ስብራት በደረሰባቸው ወገኖች የተሰማንን ጥልቅ ሐዘንም በተሰበረ ልብ እንገልፃለን ሲል በፌስቡክ ገጹ አስታውቋል።

በመ/ር ሽፈራው እንደሻው

ለተጨማሪ መረጃ የሀገረ ስብከቱን ማኅበራዊ ድረ-ገጾችን ይጎብኙ፣ like እና Join በማድረግ ይቀላቀሉ፣ ለሌሎችም ሼር ያድርጉ!!!

  1. ድረ-ገጽ:- www.addisababa.eotc.org.et
  2. ፌስ ቡክ ገጽ:- አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት/Addis Ababa Diocese
  3. ተሌ ግራም ቻናል:- t.me/AddisAbabaDiocese