በለቡ መብራት ኃይል አደባባይ የጌታችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ጥምቀት በድምቀት እየተከበረ ይገኛል
በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ በለቡ መብራይት ኃይል አደባባይ የጌታችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ጥምቀት በርካታ ምእመናን በተገኙበት በድምቀት እየተከበረ ይገኛል።
በባሕረ ጥምቀቱ እጅግ በርካታ ምእመናን ከዋዜማው ጀምሮ በስፍራው የተገኙ ሲሆን በዓሉ ሌሊት በማኅሌት ደምቆ አድሮ ንጋት ላይ ሥርዓተ ቅዳሴውን ተከናውኖ በመልአከ ጽዮን ቆሞስ አባ እስጢፋኖስ ይርጋ ትምህርተ ወንጌል ተሰጥተዋል።
የምስራቀ ፀሐይ ቅዱስ ገብርኤል ወቅድስት አርሴማ ወአቡነ አዳም አብያተክርስቲያናት ዋና አስተዳዳሪ ክቡር መልአከ ጽዮን ቆሞስ አባ እስጢፋኖስ ይርጋ “እናንተ የማታውቁት በመካከላችሁ ቆሞአል” ዮሐ. 1:26 በሚል መነሻነት በዓሉን በተመለከተ ሰፋ ያለ ትምህርተ ወንጌል ሰጥተዋል ።
በአሁን ሰዓት ታቦታቱ በበርካታ ምእመናን ታጅበው፥ በሊቃውት እና በወጣት ሰንበት ትምህርት ቤት መዘምራን የዝማሬና የመዝሙር ምሥጋና ደምቀው ወደየመጡበት አብያተ ክርስቲያናት እየተመለሱ ይገኛሉ።
በመ/ር ኪደ ዜናዊ
ለተጨማሪ መረጃ የሀገረ ስብከቱን ማኅበራዊ ድረ-ገጾችን ይጎብኙ፣ like እና Join በማድረግ ይቀላቀሉ፣ ለሌሎችም ሼር ያድርጉ!!!
- ድረ-ገጽ:- www.addisababa.eotc.org.et
- ፌስ ቡክ ገጽ:- www.facebook.com/AddisAbabaDiocese/
- ተሌ ግራም ቻናል:- t.me/AddisAbabaDiocese