ዛሬ የነጻነታችን ቀን ነው……..ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ
ዛሬ በጃን ሜዳ በድምቀት እየተከበረ ባለው የጌታችን የመድኀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጥምቀት በዓል ላይ የተገኙት ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ የአዲስ አበባና የጉራጌ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የበዓሉ መሰረቱ የእዳ ደብዳቤ እንደሆነ ገልጸው ይሄንን የተመለከተ ሰፊ ትምህርት ስጥተዋል። ይህ እዳ ደብዳቤ ተቀዶ ነጻነታችን የታወጀበት የነጻነታችን ቀን ነው ሲሉ በተጠምቀ ሰማያዊ በእደ መሬታዊ በሚል ቃለ ወንጌል መነሻ አስደግፈው በዓሉን አስመልክቶ አስተምረዋል።
አምላካችን ወደባህረ ዮርዳኖስ እንደወረደው ሁሉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ታቦታቱ ወደ ባህረ ጥምቀት ከመንበረ ክብራቸው ወጥተው ምዕመናኑን እየባረኩ ይወርዳሉ ብለዋል።
በአዲስ አበባ 265 አድባራት እንዳሉ እና 74 የጥምቀት በዓል ማክበሪያ ባህረ ጥምቀት እንዳለ ገልጸዋል። ቤተክርስቲያን ብዙ መንፈሳዊ ቅርሶች እንዳሏት የገለፁት ብፁዕነታቸው እንዲህ አይነቱን መንፈሳዊ ቅርስ ለሀገር በማበርከቷ ቤተክርስቲያን ልትመሰገን ይገባል ብለዋል።
ምዕመናን የጥምቀት በዓልን ስታከብሩ በመንፈሳዊ ጨዋነት ሆኖ ፍቅር እና ሠላምንም ወደቤታችሁ ይዛችሁ ግቡ ሲሉ በልዩ መልክታቸው አስተላልፈዋል።
በተክለሃይማኖት አዳነ
ለተጨማሪ መረጃ የሀገረ ስብከቱን ማኅበራዊ ድረ-ገጾችን ይጎብኙ፣ like እና Join በማድረግ ይቀላቀሉ፣ ለሌሎችም ሼር ያድርጉ!!!
1. ድረ-ገጽ:- www.addisababa.eotc.org.et
2. ፌስ ቡክ ገጽ:- www.facebook.com/AddisAbabaDiocese/
3. ተሌ ግራም ቻናል:- t.me/AddisAbabaDiocese