የኢትዮጵያና የኬንያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤያት የጋራ ስምምነት ተፈራረሙ !!!

በምሥራቅ አፍሪካ የቀጠናውን የሰላምና የመከባበር ዕሴት ለመገንባት እንዲሁም ጽንፈኝነትን ለመከላከል የሚያስችል የጋራ ስምምነት ሰነድ ተፈራረሙ።

ስምምነቱን የተፈራረሙት የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤና የኬንያ የሐይማኖት ተቋማት ጉባኤ ናቸው።

ስምምነቱን የኢትዮጵያ ሐይማኖት ተቋማት ጉባኤ የሥራ አስፈጻሚ ቦርድ አባላትና የኬንያ የተቋሙ ዳይሬክተርና ዋና ጸሐፊ ተፈራርመዋል።

በስምምነቱ ወቅት ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ታጋይ ታደለ ጉባኤው በምሥራቅ አፍሪካ ሀገራት ከሚገኙ የሃይማኖት ተቋማትና ድርጅቶች ጋር በትብብር ለመስራት የተለያዩ ግንኙነቶችን እያደረገ መሆኑን ተናግረዋል።

ይህ ስምምነት ለአገራዊና አካባቢያዊ ሰላምና ጸጥታ መጠበቅ የላቀ ፋይዳ ይኖረዋልም ተብሏል።

ስምምነቱ የሁለቱ ሀገራት በጋራና በትብብር የመሥራት አካል ነው የተባለ ሲሆን ወደፊትም በቀጠናው ካሉ አገራት ጋር ይህ ግንኙነት እንደሚጠናከር ተጠቁሟል።

ከዚህም በተጨማሪ ስምምነቱ ትውልድን በበጎ ለመገንባትና የዕርቀ ሰላም አጀንዳዎችን ለማስፈጸም እንደሚያስችል ነው የተነገረው።

የመረጃው ምንጭ:- ኢዜአ

በመ/ር ሽፈራው እንደሻው

ለተጨማሪ መረጃ የሀገረ ስብከቱን ማኅበራዊ ድረ-ገጾችን ይጎብኙ፣ like እና Join በማድረግ ይቀላቀሉ፣ ለሌሎችም ሼር ያድርጉ!!!

  1. ድረ-ገጽ:- www.addisababa.eotc.org.et
  2. ፌስ ቡክ ገጽ:- www.facebook.com/AddisAbabaDiocese/
  3. ተሌ ግራም ቻናል:- t.me/AddisAbabaDiocese