የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ለሦስት ቀናት ሲያካሂድ የሰነበተው ጸሎተ ፍትሐትና ምሕላ ተጠናቀቀ!!!

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰሜን ሽዋ ሀገረ ስብከት በኅልውና ዘመቻ ለሀገርና ለወገን በመዋደቅ ለተሰው የጸጥታ አባላትና በጦርነቱ የተነሣ ሕይወታቸውን ላጡ ምእመናን በደብረ ብርሃን ከተማ አጼ ዘርዐ ያዕቆብ አደባባይ ከታኅሣሥ 5 -7 ለሦስት ቀናት ሲያካሂድ የሰነበተው ጸሎተ ፍትሐትና ጸሎተ ምሕላ ተጠናቅቋል::

ለሦስት ቀናት የተካሄደውን ጸሎተ ፍትሐትና ምሕላ በሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ እና በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ በብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ መሪነት ነው።

በጸሎተ ፍትሐትና በጸሎተ ምሕላ መርሐ-ግብሩ ዓላማ መሠረት ስለ ሀገራችን ወቅታዊ ችግር ጸሎት የተደረገ ሲሆን  የሁሉም አድባራት አስተዳዳሪዎች ፣ መዘምራንና ካህናት በተገኙበት ለሀገራቸውና ለወገናቸው ሲሉ ሕይወታቸውን ለሰጡ ወገኖቻችን ጸሎተ ፍትሐት ተደርጓል።

ይኽ ጸሎተ ፍትሐትና ጸሎተ ምሕላ መርሐ-ግብር በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ የከተማዋ ነዋሪዎች ምእመናን በተገኙበት ለ3 ቀናት የተካሄደ ሲሆን “ይኽችን ከተማ አድናት ዘንድ እጋርዳታለሁ” በሚል ርእስ ያዘኑና የተከዙ የተቸገሩና በመከራ ያሉ የተራቡ የተጠሙ እንዲጽናኑ ሰፊ ትምህርተ ወንጌል በሀገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ  መጋቤ ሐዲስ ነቅዐ ጥበብ አባቡ ተሰጥቷል።

ለተጨማሪ መረጃ የሀገረ ስብከቱን የማኅበራዊ ድረ-ገጾችን ይጎብኙ፣ like እና Join በማድረግ ይቀላቀሉ፣ ለሌሎችም ሼር ያድርጉ!!!

  1. ድረ-ገጽ:- www.addisababa.eotc.org.et
  2. ፌስ ቡክ ገጽ:- www.facebook.com/AddisAbabaDiocese/
  3. ተሌ ግራም ቻናል:- t.me/AddisAbabaDiocese

     በመ/ር ሽፈራው እንደሻው