የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ ቤት በአሮጌ ቄራ ባለ 3B + G+15 ሕንጻ ሊገነባ መሆኑን ተገለጸ
የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት በአሮጌ ቄራ ባለ 3B + G+15 ሕንጻ ለመገንባት በዝግጅት ላይ መሆኑን ገልጿል
የሕንጻው ግንባታ ዲዛይን ሂደት በኢንጅነር ታምሩ ጥላሁን ለብፁዓን አባቶች ገለጻ ተደርጓል
ሕንጻው ለሀገረ ስብከቱ ዘርፈ ብዙ ጥቅም ያለውና ከ70 በላይ ፓርክ ያለው መሆኑን ተገልጿል።
በገለጻው የተገኙት የጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ሥራ አስኪያጅ ብፁዕ አቡነ ያሬድና የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ ሥራው እጅግ አስደሳችና ሀገረ ስብከቱ የራሱን የሆነ የገቢ ምንጭ የሚያገኝበት መልካም ጅምር መሆኑን በመግለጽ ትግበራ ላይ ትኩረት እንዲደረግ አሳስበዋል።
የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ መ/ር አካለ ወልድ ተሰማ ከብዙ ውይይት በኋላ ሕንጻው በዚህ ዲዛይን መሠረት እንዲገነባ ወስነናል ብለዋል።
አያይዘውም ሀገረ ስብከቱ የራሱ የሆነ መንበረ ጵጵስና የሌለው መሆኑን በመግለጽ ለዚህም መፍትሔ ለማምጣት በጥረት ላይ መሆናቸውን ገልጸዋል።
የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ በበኩላቸው የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ከአጥቢያዎቹ ፐርሰንት ውጪ ምንም ዓይነት የገቢ ምንጭ የለውም ብለዋል።
አስከትለውም እግዚአብሔር ቢፈቅድ ይህ ሕንጻ ከተገነባ በኋላ ሀገረ ስብከቱ ከፐርሰት ውጪ የራሱን የሆነ የገቢ ምንጭ እንደሚኖረው ገልጸዋል።
ዘጋቢ መ/ር ኪደ ዜናዊ
ፎቶ በመ/ር ዋሲሁን ተሾመ