የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዘመኑን በዋጀ መልኩ በአዲስ መልክ ለማደራጀት የወጣ ውስጠ ደንብ ረቂቅ ቀርቦ ውይይት ተደረገበት
ከሀገረ ስብከት እስከ አጥቢያ ያለው መዋቅራዊና አደረጃጀት የሚያጠና 13 አባላት ያሉት ኮሚቴ ያቀረበው ውሰጠ ደንብ ረቂቅ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።
በአጥኚው ኮሚቴ የቀረበው ውስጠ ደንቡ በሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ እየተመራ የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ መ/ር አካለ ወልድ ተሰማና የየዋና ክፍል ኃላፊዎች በተገኙበት ቀርቦ ውይይት ተርጎበታል።
ውስጠ ደንቡ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዘመኑን በዋጀ መልኩ ለማደራጀት የወጣ ውስጠ ደንብ ሲሆን በውስጡ አሥራ አምስት ክፍል ያሉት ደንብ ነው።
ሀገረ ስብከቱ ራሱን ችሎ በራሱ ሊቀ ጳጳስ መመራትን ተኸትሎ በአዲስ መልክ ለማደራጀት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ የቀረበ መነሻ ውስጠ ደንብ መሆኑን ተብራርቷል።
በመጨረሻም በኮሚቴው የቀረበውና ውይይት የተደረገበት የሀገረ ስብከቱ ረቂቅ ውስጠ ደንብ ለቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ቀርቦ የሚጸድቅ መሆኑን ተገልጿል።
ዘጋቢ መ/ር ኪደ ዜናዊ