የሀገረ ስብከቱ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ አጠቃቀም ትግበራ

“እንግዲህ እንደ ጥበበኞች እንጂ ጥበብ እንደሌላቸው ሳይሆን እንዴት እንድትመላለሱ በጥንቃቄ ተጠበቁ፤ ቀኖቹ ክፍዎች ናቸውና ዘመኑን ዋጁ”፡፡ ኤፌ. 5÷15

በመ/ር ዘሩ ብርሃኔ

አሁን የምንገኝበት ዘመን የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ጥቅም ጎልቶ የታየበት ዘመን በመሆኑ በዚሁ ቴክኖሎጂ ኦቶሜሽን ሲስተም ያልታገዘ አሠራር አዝጋሚ እና አድካሚ ከመሆኑም በላይ ብክነትን ባስወገደ መልኩ የሚፈለገውን ያህል  አጥጋቢ እና ውጤታማ ለመሆን ያስቸግራል። ሀገረ ስብከቱ በሥሩ ከሚገኙ ገዳማትና አድባራት ጋር ቀልጣፋ የሆነ ዘመናዊ የመረጃ ልውውጥ እንዲኖር ለማድረግ እንዲሁም ወቅታዊ እና ልዩ ልዩ ዳሰሳዎችን በተፈለገው ጊዜ እና ጥራት ለማግኘት የኢንፎርሜሽን ሲስተም መዘርጋት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ከመቸውም ጊዜ በተሻለ ሁኔታ ሁለንተናዊ የሥራ እንቅስቃሴዎቹን  በቴክኖሎጂ የታገዘ ለማድረግ በብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ የአዲስ አበባና የጉራጌ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የሚመራው የሀገረ ስብከቱ አስተዳደር ሌት ተቀን በመሥራት ላይ ይገኛል ።ይህም የሀገረ ስብከቱን አቅም ግንባታ በማሳደግ የተቀላጠፈ እና ከስህተት የጸዳ አገልግሎት ለመስጠት ያስችለዋል። ሀገረ ሰብከቱ ይህን ቴክኖሎጂ በመጠቀም ዓላማውን ሙሉ በሙሉ ከማሳካቱም ባሻገር በሥራ ዓለም ውስጥ ብቁና ተወዳዳሪ እንዲሆን ያደረገዋል፡፡

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሥር ካሉ 50 አህጉረ ስብከት መካከል በተደራጀ መልኩ ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ በመጠቀም አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የመጀመሪያው ነው፡፡አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዘመኑ ያስገኘውን ቴክኖሎጂ በመጠቀም አገልግሎቱን የበለጠ ለማሳደግና በመላው ዓለም ስርጭቱን ተደራሽ እንዲሆን ታስቦ  እጅግ ዘመናዊ የሆነ  ይፋዊ(ኦፊሻል) ድረ-ገፅ አዘጋጅቶ ሥራ ላይ እንዲውል አድርጓል፡፡

የዚሁ ቴክኖሎጂ አገልግሎትም ዘመኑ ባስገኘው  ቴክኖሎጂ በመጠቀም ስብከተ ወንጌልን ፤ የቤተ ክርስቲያናችንን አስተምህሮ እና የቤተ ክርስቲያኒቱን ማኅበራዊ አገልግሎቶች ለዓለም ሕዝብ በማዳረስ ዓይነተኛ መሣሪያ ሆኖ አገልግሎት መስጠት ሲሆን በተጨማሪም ድረ ገጹን  በመጠቀም የቤተ ክርስቲያናችንን አኩሪ ታሪክ ቅርስና ታሪካዊ ቦታዎችን  ከማስተዋወቅ ባሻገር ወቅታዊ የሆኑ መረጃዎችን ፤ዕቅዶችን እና  የሥራ አፈጻጸም ሪፖርቶችን ለኢትዮጵያ ኦርቶዶከስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት ተከታዮች በቀላሉ እንዲዳረስ በማድረግ በኩል ከፍተኛ የሆነ የግልፅነትና የተአማኒነት ሚና እንዲጫወት ማድረግ ነው ፡፡

የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሥራ አንዴ ተሠርቶ የሚያልቅ ሥራ ባለመሆኑ ሀገረ ስብከቱ በብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ የአዲስ አበባና የጉራጌ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ መመሪያ ሰጭነትና መሪነት ወቅታዊ የሆኑ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን/ሲስተሞችን አዘጋጅቶ ሥራ ላይ አውሏል፡፡ ለተሠሩት ሲስተሞች ግብዓት የሚሆኑ የሰው ኃይል እና የንብረት ሀብት መረጃ የሚሰበስቡ ኮሚቴዎች አዋቅሮ ከ170 በላይ ገዳማትና አድባራት መረጃ ተሰብስቦ ወደ ሥራ ተግብቷል፡፡የሀገረ ስብከቱ አይቲና ዶክሜንቴሽን ክፍሉን በአግባቡ ከማደራጀት ጀምሮ የተሻሉ የቴክኖሎጂ ሥራዎችን ለመሥራት በሙሉ አቅም ላይ ይገኛል፡፡

በሀገረ ስብከቱ ከተሠሩ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሥራዎች መካከል፡-

  1. የሰው ሀብት አስተዳደር ሲስተም/ Human Resource management system 
    1. የንብረትና ሀብት አስተዳደር ሲስተም/ Asset Management System
    1.  የመዝገብ ቤት ፋይል አስተዳደር ሲስተም/Archive File Management system
    1. እስቶክ አስተዳደር ሲስተም/ Stock Management System
    1. ድረ ገጽ∕ ዌብ ሳይት፣ ማኅበራዊ ፌስ ቡክ ገጽ፣ዩትዮብ ቴሌግራም ቻናል/ Web site, Face book page እና
    1. የሀገረ ስብከቱ ሕንፃ ኔትዎርክ ዝርጋታ፣ የ20 ሜጋ ባይት ብሮድባንድ ኢንተርኔት እና ዋይ ፋይ(Wi- Fi)  አገልግሎት ከብዙ በጥቂቱ ናቸው፡፡

ሲስተሞቹ የሚሰጧቸው  አገልግሎቶች በከፊል

1የሰው ሀብት አስተዳደር ሲስተም/ Human Resource management system: – ይህ ሲስተም የሀገረ ስብከቱን፣ የክፍላተ ከተማዎችንና የአዲስ አበባ ገዳማትና አድባራት ሠራተኞች ሙሉ መረጃ መዝግቦ በመያዝ፤ ሥራው የሚመለከታቸው የሀገረ ስብከቱ ኃላፊዎች መረጃዎችን ለማግኘት ቀጥታ በአካል መሄድ ሳያስፈልጋቸው ባሉበት ቦታ ሆነው በተመሳሳይ ሰዓት የተለያዩ ዶክሜንቶችን በተፈለገው ሰዓት የሚፈልጉትን መረጃ በጥራትና በፍጥነት ለማግኘት የሚያግዝ በጣም ፈጣንና አስተማማኝ የሆነ ሲስተም ነው፡፡ ይህም የሰው ኃይል፣ጊዜ፣ገንዘብ፣ጉልበት፣ድካም እና የተለያዩ ስጋቶችን ይቀንሳል፡፡

2.   የንብረትና ሀብት አስተዳደር ሲስተም/ Asset Management System: – ይህ ሲስተም የሀገረ ስብከቱን፣ የክፍላተ ከተማዎችንና የአዲስ አበባ ገዳማትና አድባራት ንብረትና ሀብት (ሕንፃ፣ መሬት፣ መኪና እና የተለያዩ የይዞታ ካርታዎች ወዘተ…) ሙሉ መረጃ መዝግቦ የሚይዝ ሲስተም ነው፡፡

3. የመዝግብ ቤት ፋይል አስተዳደር ሲስተም/ File Management system:-ይህ ሲስተም እስከ አሁን የነበረውን ባህላዊ/Manual/ የሀገረ ስብከቱ ሪከርድ ክፍል አሠራር ወደ ዘመናዊ/ Computerized System በመቀየር በልምድ ይከናወን የነበረውን አሠራር ከመቅረፉም በላይ ሥራው ከሀሜት በፀዳ መልኩ እንዲሠራ ይረዳል፤ በዚህም መሠረት እስከ አሁን በሀገረ ስብከቱ የተሠሩት እና ወደ ፊትም የሚሠሩትን ሥራዎች ሁሉ ወደ አዲሱ መረጃ ቋት/ሲስተም/ከገባ በኋላ የተለያዩ የመፈለጊያ መንገዶችን በመጠቀም በአጭር ጊዜ ውስጥ የተለያዩ አገልግሎቶችን ማግኘት የሚያስችል ሲስተም ነው፡፡

4. የአላቂ ዕቃዎች ዕቃዎች አስተዳደር ሲስተም/ Stock Management System

አጠቃላይ የሀገረ ስብከቱ አላቂ ዕቃዎች ዝርዝር መዝግቦ የሚይዝ ሲስተም ሲሆን ይህ  የቴክኖሎጂ ሲስተም ሀገረ ስብከቱ የሚሰጠውን አገልግሎት በዘመናዊ የኮምፒዩተር ቴክኖሎጂ የታገዘና አንድ ማዕከላዊ በሆነ ኮምፒዩተር/ሰርቨር/ ላይ ሲስተሙ በመጫን በLocal Area Network IP Address አማካኝነት ሥራው የሚመለከታቸው አካላት በሀገረ ስብከቱ ያሉ ኮምፒዩተሮችን በመጠቀም ባሉበት ቦታ ሆነው በንብርት ክፍል ያሉትን ኣላቂ ዕቃዎች ዝርዝር በቀላሉ መቆጣጠር /ማስተዳደር የሚችሉበት ሲስተም ነው፡፡

5. ድረ ገጽ∕ ዌብ ሳይት∕ Web site እና ፌስቡክ ገጽ

ይህ ቴክኖሎጂ በየቀኑ፡-

  1. ወቅታዊ መረጃዎችን/ዜናዎችን/ ለአንባቢዎች ያደርሳል፤
  2. የሀገረ ስብከቱ መንፈሳዊና ማኅበራዊ አገልግሎቶችን ለዓለም ሕዝብ ያሰራጫል፤
  3. በሀገረ ስብከቱ እንዲሁም በአጠቃላይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን የተመለከቱ መግለጫዎችን፤ ለበዓላት የሚተላለፉ መልእክቶችን እንዲሁም ሌሎች ልዩ ልዩ መረጃዎችን ለሕዝበ ክርስቲያኑ በማቅረብ ላይ ይገኛል፡፡

የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሥራ አንዴ ተሠርቶ የሚያልቅ ሥራ  ባለመሆኑ  ሀገረ ስብከቱ ተጨማሪና ወቅታዊ የሆኑ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን/ሲስተሞችን/ አዘጋጅቶ ሥራ ላይ ለማዋል በዝግጅት ላይ ይገኛል፡፡