በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል የብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ 8ተኛ ዓመት መታሰቢያ ምክንያት በማድረግ ለተቸገሩ ህጻናት እርዳታ ተሰጠ
ነሐሴ 10/2012 ዓ.ም በቅዱስነታቸው የመንፈስ ልጆቻቸው የተቋቋመው ፍቅረ ገብርኤል የወንድማማቾች ማኅበር በተባለ በጎ አድራጊ ማኅበር በካቴድራሉ ምግባረ ሠናይ ክፍል አስተባባሪነት በካቴድራሉ አካባቢ ለሚገኙ ተረጂ ህጻናት ለእያንዳንዳቸው 500 ብር፣ 10 ኪሎ ፍርኖ ዱቄት፣ 5 ሌትር ዘይት፣ 5 እሽግ ፓስታ፣ 5 ሳሙና 1 የትምህርት ቤት የተማሪዎች ቦርሳ፣ 1 ደርዘን ደብተር፣ 5 እስክሪብቶ፣ 3 ላጲስ፣ 3 እርሳስ መቅረጫ እና 5 እርሳስ እርዳታ ተሰጥቷዋል ።
ፍቅረ ገብርኤል የወንድማማቾች ማኅበር በ2011ዓ.ም በዚሁ ዕለት ተመሳሳይ የትምህርት እርዳታ ለተረጂ ህጻናቱ ድጋፍ አድርጎ እንደነበር ይታወሳል።
በዛሬው ዕለት 5ተኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ የነበሩት የብፁዕ ወቅዱስ ዶ/ር አቡነ ጳውሎስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት የዓለም ሃይማኖቶች የሠላም የክብር ፕሬዚዳንት 8ተኛ ዓመት የዕረፍታቸው መታሰቢያ በዓል በመላው ኦርቶዶክሳውያን ታስቦ የዋለ ሲሆን በተለይም በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በጸሎተ ቅዳሴና ጸሎተ ፍትሐት ታስቦ ውሏል።
በመ/ር ዘሩ ብርሃኔ(MA)