21ኛው ክፍለ ዘመን እና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ የቤተ ክርስቲያን የሚዲያ አጠቃቀም

በመ/ር ዘሩ ብርሃኔ (MA) የሀገረ ስብከቱ

አይቲና ዶክሜንቴሽን  ክፍል ኃላፊ

እንደየ ዘመኑ አጠራርና አተገባበር ይለያይ እንጂ የሚዲያ አጠቃቀም ለቤተ ክርስቲያን አዲስ ነው ለማለት ባያስደፍርም ከቤተ ክርስቲያኒቱ ዓለም አቀፍ ሐዋርያዊ አገልግሎት አንፃር ሲታይ ሚዲያው ምን ያህል እንገለገልበታለን የሚለው ጉዳይ ግን አነጋጋሪ ነው፡፡ቤተ ክርስቲያኒቱ ቀደም ሲል በፕሪንትሚዲያ(ጋዜጣና መጽሔት…) በኋላም በተወሰነመልኩ ለስብከተ ወንጌል አገልግሎት የሚውል ኤሌክትሮኒክስ ሚዲያ(ሬድዮ) ትጠቀም እንደነበር የታሪክ መዛገብት ያስረዳሉ፡፡ይሁን እንጂ አሁን ባለንበት ክፍለ ዘመን ኤሌክትሮኒክስ ሚዲያ /ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ(ማኅበራዊ ድረ-ገፅ፤ሳተላይት ቴሌቪዥን እና ሬድዮ) በተደራሽነቱ፤በዓለም አቀፍ ስርጭቱ፤በዋጋ ቅናሽነቱ እና ዓለምን ወደ አንድ መንደር በማምጣት በከፍተኛ ፍጥነት በማደግ ላይ ይገኛል::

ዝርዝሩን በPDF ለማንበብ እዚሁ ላይ ይጫኑ