የአዲስ አበባ ገዳማትና አድባራት የሒሳብ ሠራተኞች የ1ና የ2ኛ ዙር ሥልጣኞች ወደ ተግባር የሚያስገባ ተጨማሪ ሥልጠና እየተሰጣቸው ነው
በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሥር የሚገኙ የገዳማትና የአድባራት የሒሳብ ሠራተኛች ቀደም ሲል በሀገረ ስብከቱ በተዘጋጀው የሥልጠና ማዕከል ከ2ወራት በላነሰ ሲሰለጥኑ የቆዩ ሲሆን ይህንኑ የሙያ ማሻሻያ ሥልጠና ወደተግባር የሚያስገባ ለ4 ተከታታይ ቀናት የሚቆይ የሒሳብ ሥራ ሥልጠና በተጋባዥ ባለሙያዎች እየተሰጣቸው መሆኑ ተረጋግጧል፡፡
አብዛኞቹ ሠልጣኞች በአካውንቲንግ የመጀመሪያ ድግሪ ያላቸው ሲሆን የተወሰኑት ሠልጣኞች በቲኦሎጂ በዲኘሎማና በድግሪ መርሐ ግብር ተመርቀዋል፡፡
የስልጠናው ይዘትም በገንዘብ አያያዝና በንብረት አመዘጋገብ ላይ የተመሠረተ ነው÷ ስልጠናው በአካውንት ወሳኝ ነጥብ ላይ ትኩረት ይደረጋል፤ በስልጠናው የሚገኘው ጥቅም ቀደም ሲል ሠልጣኞቹ በስፋት የተማሩት ከመሆናቸው አንጻር ወደተግባር ለመግባት እንደማያስቸግራቸው በአሰልጣኝ ባለሙያው ተብራርቱል፡፡
ስልጠናው በእስላይድ የታገዘ በመሆኑ ለሰልጣኞቹ የግንዛቤ ማስጨበጫ ዕውቀት ጉልህ አስተዋጽኦ ይኖረዋል፡፡ በአሰልጣኙ እንደተብራራው ይህ ሒሳብ ሥራ መመሪያና በሒሳብ መዋቅርና ፖሊሲ ላይ ያተኩራል÷ በካሽና በቼክ ስለሚከፈል ገንዘብና በባንክ ስለሚቀመጥ ገንዘብ እንደዚሁም ስለንብረት አመዘጋገብ በተለይ የሚጋጩ የሚመስሉ የሒሳብ አሠራሮችን እንዴት ማስታረቅና ማስማማት እንደሚችል፣ በንብረት ገቢና ወጪ ደጋፊ ሰነዶች ላይ በመንግሥትና በአትራፊ ተቋማት እየተሠራበት ስላለው ደብል ኢንትሪ በቂ ማብራሪያ ይሰጣል÷ የሲንግል ኢንትሪና የደብል ኢንትሪ ልዩነት እንዴት እንደሚታይ በሥልጠናው ተገልጿል÷ በተጨማሪም ስለሪፖርት አቀራረብና ስለዶክመንት አያያዝ፣ ስለሒሳብ ምርመራ በስልጠናው ይዳሰሳል፡፡ ይህ የተግባር ሥልጠና ከግንቦት 3 ቀን 2008 ዓ.ም እስከ ግንባት 6 ቀን 2008 ዓ.ም ለ4 ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ሲሆን በሥልጠናው ላይ የሚሳተፉ የሠልጣኞች ቁጥር 60 የሒሳብ እና 60 የቁጥጥር ባሞያዎችን ያካተተ ነው ፡፡በሥልጠናው መክፈቻ ላይ የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ መምህር ጎይቶም ያይኑ ባስተላለፉት መልእክት ይህ ሥልጠና የቤተ ክርስቲያናችንን የሒሳብ አያያዝና የንብረት አመዘጋገብ ችግር ስለሚፈታ ሀገረ ስብከቱ ለስልጠናው አስፈላጊውን ድጋፍ ይሰጣል ብለዋል፡፡
በቀጣይም የ3ኛ ዙር ሥልጣና ከግንቦት 2008 አጋማሽ ጀምሮ የሚጀመር ሲሆን የሞዴላ ሞዴል ህትመት ዘግጅትም ተጠናቅቆ በማለቁ ከሐምሌ1/2008 ጀምሮ በአዲሱ ሞዴል ሥራ እንደሚጀመር ለማወቅ ተችሏል፡፡
ይህ ሥልጠና የተሰጠው ሀገረ ስበከቱ የፓትርያርኩ ልዩ ሀገረ ስብከት በመሆኑ ከቅዱስነታቸው በተገኘ መልካም ፈቃድ መሆኑን ለመወቅ ተችሏል፡፡