የምሥራቀ ፀሐይ ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን የልማት እንቅስቃሴ

g0021

የምሥራቀ ፀሐይ ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ቤተክህነት ሥር የሚገኝ ሲሆን ይህ ቤ/ክ በ1986 ዓ.ም በአካባቢው ምዕመናን ተመሠረተ፡፡ የቤተክርስቲያኑ የይዞታ ቦታ 79,571 ካሬ ሜትር ስፋት አለው ሲሆን በቤተክርስቲያኑ በልዩ ልዩ የሥራ መስክ የተመደቡ ሠራተኞች ብዛት 93 ናቸው፡፡
በቤተ ክርስቲያኑ እየተሠሩ የሚገኙ የልማት ሥራዎች
በ3,310 ካሬ ሜትር ስፋት ላይ ያረፈ ሕንጻ ቤተክርስቲያን ግንባታ፤ለአስራ ሁለት ግለሰቦች ተከራይቶ በወር 157,332 ወርሐዊ የገንዘብ ገቢ የሚአስገኝ ባዶ ቦታ ፤በካሬ ሜትር 5 ብርና 8 ብር ተከራይቶ በወር 35,872 የገንዘብ ገቢ የሚአስገኝ ባዶ ቦታ፤ ለእንጨት መሰንጠቂያ በወር 3,900 ብር የተከራየ ቦታ ይገኝበታል፡፡
በቤተክርስቲያኑ ሊሠሩ የታቀዱ የልማት ሥራዎች
በአቅራቢያው የሚገኘውን የቅድሥት አርሴማን ቤተክርስቲያን በ1,000 ካሬ ሜትር ስፋት ላይ መገንባት፤ ተጨማሪ ይዞታን ለማስፋፋት የካርታ ማሠራት ሥራ፤ የግቢ ማስዋብ ሥራ፤ የስብከተ ወንጌል አዳራሽ ግንባታ፤ የሆስፒታል ግንባታ ሥራ እና የተጀመረውን ሕንጻ ቤተክርስቲያን ማስፈጸም ነው፡፡