በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ ተልዕኮ ዋና ክፍል የወጣ ክፍት የሥራ ማስታወቂያ

640

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሲሠራበት የነበረውን ለማዳዊ አሠራር ወደ ዘመናዊ የአስተዳደር ሲስተም መቀየሩን ተከታትሎ አመርቂ ውጤት ከተገኘባቸው የሥራ አይነቶች መካከል የሠራተኛ ቅጥርና ዝውውር እንዲሁም የዕድገት አሰጣጥ ግንባር ቀደም ተጠቃሽ ነው፡፡
ሀገረ ስብከቱ መልካም አስተዳደርን ለማስፈን በወሰዳቸው እርምጃዎች ካለፈው መጋቢት ወር ጀምሮ መምህራንን፣ ካህናትንና ዲያቆናትን አወዳድሮ መቅጠር በመጀመሩ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንና ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ብሎም ምእመናን ተጠቃሚዎች መሆናቸው አያጠያይቅም፡፡
አሁንም ሀገረ ስብከቱ በሥሩ ባሉ አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት ሰባክያነ ወንጌልን አወዳድሮ መቅጠር ስለፈለገ፣ መስፈርቱን የምታሟሉ እና መወዳደር የምትፈልጉ በተጠቀሰው ቀን መጥታችሁ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እያሳሰብን፣ የሀገረ ስብከቱ የስብከተ ወንጌል እና ሐዋርያዊ ተልዕኮ ዋና ክፍል ያወጣውን ማስታወቂያ ከዚህ እንደሚከተለው አቅርበናል፡፡

 

                                                                 የካቲት 4 ቀን 2008 ዓ.ም
ክፍት የሥራ ቦታ ማስታወቂያ
የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በሥሩ ባሉት አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት ባለው ክፍት የስብከተ ወንጌል ሥራ ሰባክያነ ወንጌልን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ:-
1. በቤተ ክርስቲያንዋ ጉባዔ ቤት እና መንፈሳዊ ኮሌጆች ተምሮ የተመረቀና የትምህርት ማስረጃውን ማቅረብ የሚችል፤
2.ከዚህ ቀደም በማንኛውም ደረጃ የሃይማኖት ሕፀፅ ተጠርጥሮ ያልተከሰሰ ወይም ከዚህ ጋር በተያያዘ ምክንያት ከስብከተ ወንጌል አገልግሎት ያልተከለከለ (ያልታገደ)፣
3.እስከአሁን ሲያገለግል ከነበረበት ቤተ ክርስቲያን ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፣
ስለዚህ መሥፈርቱን የምታሟሉና መወዳደር የምትፈለጉ በሀገረ ስብከቱ ስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ ተልዕኮ ክፍል ቢሮ ቁጥር 211 ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ የካቲት 15/2008 ዓ.ም ድረስ ማስረጃችሁን በማያዝ ዋናውንና የማይመለስ ፎቶ በማያያዝ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን የፈተናው ቀን በቀጣይ ማስታወቂያ የሚገለጽ መሆኑን እናስታውቃለን፡፡
                                                                 ጽ/ቤቱ

{flike}{plusone}