የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት ለአህጉረ-ስብከትና ለቤተ ክርስቲያናችን ተቋማት እገዛ እያደረገ ነው

00230
የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ህንፃ በከፊል

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ራሱ ካለበት ዘርፈ ብዙ ሥራዎች በተጨማሪ የቤተ ክርስቲያንን ሁለንተናዊ ዕድገት ለሚያፋጥኑ እንዲሁም ወቅታዊ ችግር ላለባቸው አህጉረ ስብከትና የልማት ተቋማት ድጋፍ እያደረገ መሆኑ ተገለፀ፡፡ የሀገረ ስብከቱ ጽ/ቤት ባለፉት 6 ወራት ብር 8,000,000.00 (ስምንት ሚሊየን ብር) የሚጠጋ ድጋፍ ማድረጉ ታውቋል፡፡
ድጋፍ ከተደረገላቸው ውስጥ በብፁዕ አቡነ ሉቃስ ለሚመራው የሰቲት ሑመራ ሀገረ ስብከት፣ የብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ ሀገረ ስብከት ለሆነው ምስራቃዊ ትግራይ ሀገረ ስብከት፣ እንዲሁም የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ከብር 300,000.00 (ሦስት መቶ ሺህ ብር) እስከ ብር 6,000,000.00 (ስድስት ሚሊየን ብር) የሚጠጋ በነፍስ ወከፍ ድጋፍ እንደተደረገላቸው ታውቋል፡፡
በተጨማሪ ሰብአዊ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው መቄዶንያ የአረጋውያንና የአእምሮ ሕሙማን ማዕከልና ሰው ለሰው የተባለ የቀድሞ መንግሥት ባለሥልጣናት መረዳጃ ማህበር ከብር 50,000.00 – 100,000.00 ብር ድጋፍ የተደረገላቸው መሆኑን ዋና ሥራ አስኪያጁ ሊቀ ማእምራን የማነ ዘመንፈስ ቅዱስ ገልፀዋል፡፡
በቀጣይ ለሌሎች አህጉረ ስብከት እና ድጋፍ ለሚሹ አካላት በቋሚነት ድጋፍ የሚደረግበት ሁኔታ በሀገረ ስብከቱ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ እንዲጠና መወሰኑንም አስረድተዋል፡፡

{flike}{plusone}