የቅዱስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ለአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የምስጋና ደብዳቤ አስተላለፈ!!
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ አስተዳደር ኮሌጁን ወደ ዩኒቨርሲቲ ለማሳደግ በማሰብ እያስገነባው ለሚገኘው ታሪካዊ፣ ዘመናዊና ሁለገብ ግዙፍ ሕንፃ የገንዘብ ድጋፍ ለማድረግ የብር 6,000,000.00 (ስድስት ሚሊዮን ብር) ክፍያ እንዲፈጸም ከአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የተላለፈውን መመሪያ ተግባራዊ በመሆኑ ታህሳስ 7 ቀን 2008 ዓ.ም ኮሌጁ ለአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ምስጋና ያቀረበ ሲሆን በአጠቃላይ ከሀገረ ስብከቱ እንዲሁም ከገዳማትና አድባራት ከ20,000,000 ያላነሰ የገንዘብ ድጋፍ እንደሚደረግ ይገመታል፡፡
ከዚህ ቀጥሎ ኮሌጁ ለሀገረ ስብከቱ የጻፈው ደብዳቤ እንደሚከተለው ይነበባል፡፡
በሌላ ዜና በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በደቡብ ኦሞ ሀገረ ስብከት የስብከተ ወንጌል ማስፋፊያ ልማትና ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን አሠሪ ኮሚቴ በቁጥር ደኦ/ስልቤክአኮ/3/54/08 በቀን 10/02/08 ዓ.ም በተጻፈ ደብዳቤ ለሀገረ ስብከቱ ተመሳሳይ ምስጋና አቅርቧል፡፡
ኮሚቴው ባቀረበው የምስጋና ደብዳቤ ሀገረ ስብከቱ “ለዚህ ትልቅ አገልግሎት የምንገለገልበት ቢሮ ከ2004 ዓ.ም ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ ለ36 ወራት በነፃ መጠቀም ችለናል፡፡ ይህም ወደ ገንዘብ ሲቀየር 36×3.057 = 110,000.00” ነው፡፡
ይህ ገንዘብ ለደቡብ ኦሞ ሀገረ ስብከት ለስምንት የካህናት ቅጥር ለሦስት ዓመታት ደመወዝ የሚሸፍን ነው፡፡ በተጨማሪም በዚሁ ሕንፃ በሚገኝ የመሰብሰቢያ አድራሻ ለ12 ጊዜያት በነፃ እንድንገለገል የተፈቀደልን ሲሆን ይህም ወደ ገንዘብ ሲቀየር 12×12,000 = 24,000.00 ብር ነው፡፡
በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በሚገኙ ገዳማትና አድባራት ጉባኤያት እንድንዘረጋ፣ አውደ ርዕይ እንድንከፍት፣ የቅስቀሳ ሥራዎችን እንድንሠራ በመፍቀድ፣ የተሠሩ ሥራዎችን ለመወሰን ከመደበኛ የሥራ ሰዓት ውጭ በሳምንት አንድ ቀን እስከ ምሽቱ 1፡30 በቢሮ መሰብሰብ እንድንችል በመፍቀድ፣ እንዲሁም ኮሚቴው የሚሠራቸውን ሥራዎች በቅርበት በመከታተል ዕውቅናና ድጋፍ በመስጠት ላደረገልን አስተዋፅኦ ምስጋናችንን እናቀርባለን በማለት የምስጋና ደብዳቤያቸውን አቅርበዋል፡፡
ከዚህም በተጨማሪ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በመላው ሀገራችን በሚገኙ አህጉረ ስብከት የበጀት ድጋፍ እያደረገ የሚገኝ መሆኑ ይታወቃል፡፡
{flike}{plusone}