ሰበር ዜና
የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በሽልማት የተበረከተለትን ጄነሬተር ለአዲግራት ሀገረ ስብከት በስጦታ አስተላለፈ፡፡
የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ባስመዘገበው ከፍተኛ የሥራ ውጤት በ34ኛ መደበኛ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ በሽልማት የተበረከተለትን የመብራት ጄነሬተር በርካታ ገዳማት ለሚገኙበት ለአዲግራት ሀገረ ስብከት በስጦታ አስተላልፏል፡፡
የሰበካ ጉባኤ ማደራጃ መምሪያ ለጉባኤው ታዳሚዎች ባዘጋጀው የእራት ግብዣ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ ሊቀ ማእምራን የማነ ዘመንፈስ ቅዱስ በሰጡት ማብራሪያ ሀገረ ስብከቱ ባስመዘገበው ከፍተኛ የሥራ ውጤት በታላቁ ጉባኤ ልዩ ተሸላሚ በመሆን ሞገስ በማግኘቱ ልባዊ ደስታ የተሰማቸው መሆኑን ከገለፁ በኋላ ሽልማቱ ለወደፊቱ የተሻለ የሥራ ውጤት ለማስመዝገብ በር ከፋች ነው ብለዋል፡፡
ለሀገረ ስብከቱ በሽልማት የተበረከተውን ጄነሬተር በተመለከተም በርካታ ገዳማትን ለሚያስተዳድረው ለአዲግራት ሀገረ ስብከት በስጦታ እንዲተላለፍ ሀገረ ስብከቱ የፈቀደ መሆኑን በመግለጽ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ፣ ብፁዓን አባቶችና በጉባኤው ተሳታፊ ፊት የርክክቡ ሥነ ሥርዓት ተፈጽሟል፡፡
{flike}{plusone}