የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ባስመዘገበው ከፍተኛ የሥራ ውጤት ልዩ ተሸላሚ ሆነ!!!

00401

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስተያን በተካሄደው 34ኛ መደበኛ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ላይ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ከ2006 ዓ.ም  በ2007 የበጀት ዓመት የጠቅላይ ቤተ ክህነት ድርሻ ከሆነው 65% ብር  16,445,189.90  ብልጫ በማሳየቱ አጠቃላይ መደበኛ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ በተጠናቀቀበት ወቅት ልዩ ተሸላሚ ለመሆን በቅቷል፡፡
ይህ ከፍተኛ ውጤት ሊመዘገብ የቻለው ከሚያዝያ ወር 2007 እስከ ሐምሌ ወር 2007 ዓ.ም የበጀት ዓመት መሆኑ በሁኤው ላይ በቀረበው ሪፖርት ተገልጿል፡፡
የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በዚህ ዓመት በከፍተኛ ጥረት የተተከሉትን 5 አዳዲስ አብያተ ክርስቲያናት ጨምሮ 171 ገዳማትና አድባራትን እና 7 ክፍላተ ከተማን መሠረት በማድረግ ካለፈው ዓመት የተሻለ ሥራ ለመሥራት ከፍተኛ ጥረት አድርጓል፡፡
በ34ኛ መደበኛ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ የቀረበውን ሪፖርት በቀጣይ እናቀርባለን፡፡

{flike}{plusone}