እርሱን ስሙት የሚል ድምጽ መጣ
“ከስድስት ቀን በኋላ ኢየሱስ ጴጥሮስንና ያዕቆብን፣ ወንድሙንም ዮሐንስን ይዞ፣ ወደረጅም ተራራ ብቻቸውን አወጣቸው÷ በፊታቸውም ተለወጠ÷ ፊቱም እንደፀሐይ በራ÷ልብሱም እንደበርሃን ነጭ ሆነ÷እነሆም ሙሴና ኤልያስ ከእርሱ ጋር ሲነጋገሩ ታዩአቸው፡፡ ጴጥሮስም መልሶ ኢየሱስን ጌታ ሆይ በዚህ መሆን ለእኛ መልካም ነው ፣ብትወድስ በዚህ ሦስት ደስ አንዱን ላንተ፣አንዱንም ለሙሴ፣አንዱንም ለኤልያስ እንሥራአለ፡፡
እርሱም ገና ሲናገር እነሆ ብርሩህ ደመና ጋረዳቸው÷እነሆም ከደመናው በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው እርሱን ስሙት የሚል ድምፅ መጣ” ማቴ /17÷1 1-6/ / ማር /9÷2/ /ሉቃስ 9÷27/ ከላይ እንደተመለከትነው ቅዱስ ማቴዎስ ጌታችንና መድኃኔታችን ኢየሱሱ ክርስቶስ ብርሃነ መለኮቱን የገለፀበትን ምስጢር ሲአብራራ በስድስተኛው ቀን ብሎ ጀመረ፡፡ እንደ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ በተክርስቲያን ሥርዓተ አስተምህሮ ስድስተኛው ቀን ተብሎ የተጠቀሰው በማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ አስራ ስድስት ላይ ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶሽ ደቀ መዛሙርቱን ሰብስቦ “ የሰውን ልጅ ማን ይሉታል ? “ የሚለውን ጥያቄ በጠየቀበት በስድስተኛው ቀን ተብሎ ይገለፃል ወይም ይብራራል የመጽሐፍ ቅዱስ መምህራን ደግሞ ከመጀመሪያው ቀን ከዕሁድ ጀምሮ እስከ አርብ ድረስ ቆጥረው በስድስተኛው ቀን የሚለውን አርብ ነው ብለው ይገልፃሉ በወንጌላዊው በቅዱስ ማቴዎስ የተገለፀው ሌላው ኃይለ ቃል ወደ ተራራ ይዞአቸው ወጣ የሚል ነው፡፡ ቅዱስ ማቴዎስ የገለፀው ተራራ ታቦር ወይም አርሞንኤም እንደሆነ ይተረካል፡፡
ታቦር
ታቦር የሚባለው ተራራ ከገሊላ ባህር በምዕራባዊ ደቡብ በኩል አስር ኪሎ ሜትር ርቆ የሚገኝ ተራራ ነው፡፡ የተራራው ከፍታ ከባህር ወለል /ጠለል/ እስከ 572 ሜትር ከፍ እንደሚል ይነገራል በዚህ ተራራ ባርቅሲሣራን አሸነፈ /መሳ 4÷6/ ሳኦል በነቢዩ ሳሙኤል ትንቢት መሠረት ከ3ሰዎች ጋር በዚህ ተራራ ተገኘ /1ሳሙ10÷3/ ታቦር በዛብሎን ዕጣውስጥ ያለ ለሚራር ልጅች የተሰጠ ቦታ ነው ጌታችንእና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህ ተራራ ላይ ክብሩንና ብርሃነ መለኮቱን እንደገለጠ ብዙ ክርስቲያኖች ያምናሉ ፡፡/ ማቴ 17÷1/
አርሞንኤም
አርሞንኤም እየተባለ የሚጠራው ተራራ በሶርያ ÷ በሊባኖስና በእስራኤል ድንበር ላይ ያለው ተራራ ሲሆን የተራራው ከፍታ ከባህር ጠለል /ወለል/ እስከ 2777 ሜትር ከፍ ስለሚል በአቅራቢያው ካሉት ተራራዎች ከፍታአለው፡፡
ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ክብሩንና ብርሃነ መለኮቱን የገለጠው በዚህ ተራራ ሳይሆን እንዳልቀረ የመጽሐፍ ቅዱስ መምህራን ያምናሉ ነቢዩ ዳዊት የታቦርና የአርሞንኤም ትሪራዎች የደስታና የክብር ቦታዎች መሆናቸውን ሲገልፅ ታቦር ወአርሞንኤም በስመ ዚአከ ይትፌስሑ፡፡ ታቦርና አርሞንኤም በስምህ ደስ ይላቸዋል/መዝ88 ÷ 12/ ይላል፡፡ በአብዛኞቹ ሊቃውንት ትንታኔ መሠረት ጌታ ክብሩንና ብርሃነ መለኮቱን የገለፀበት ተራራ ደብረ ታቦር በመሆኑ ይስማማሉ፡፡ ምክንያቱ የታቦር ተራራ በእስራኤል ግዛት ውስጥ ሲሆን ጌታችንና መድኃኔታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያገለገለው በእስራኤል ግዛት ውስጥ ነው፡፡
ስለዚህ ክብሩንና ብርሃነ መለኮቱን የገለፀበት ተራራ የታቦር ተራራ ነው ይላሉ፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ከዓለም የሚጐርፉ በርካታ ጐብኙዎች የሚጎበኙት የታቦርን ተራራ ሲሆን ግሪኮችና ካቶሊኮችም በዚህ ተራራ ላይ ቤተክርስቱያን ሠርተዋል፡፡ የአርምንኤም ተራራ በሊቃውንቱ ሲገለጽ የዮርዳኖስ ወንዝ መነሻ አርሞንኤም ነው÷ ስለዚህ ታቦርና አርሞንኤም በስምህ ይደሰታሉ የተባለው ከዚህ አንፃር ነው÷ ከስድስት ቀን በኋላ ጴጥሮስ፣ያዕቆብና ዮሐንስ የጌታችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ መልክ ወደ አንፀባራቂ ብርሃናዊ ክብር ሲለወጥ አዩ፡፡ የኢየሱስ ክርስቶስ መሲሕ መሆኑን በእርግጥ መስክረዋል፡፡ /ማር 8÷29/ አሁን ደግሞ የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑን ከእነርሱ ውስጥ ለሦስቱ ደቀመዛሙርት በመገለጥ እምነታቸውን አፀናላቸው፡፡ ነቢዩ ሙሴና ኤልያስም በክብር ተገልጠዋል ከዚህ የምንረዳው የእግዚአብሔር ቅዱሳን እንዳንቀላፉ እንጂ /1ተሰ 4÷13/ እንዳልሞቱ በማያጠራጥር ሁኔታ መገንዘብ እንችላለን፡፡ ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከእንቅልፍ ያነቃቸዋል፡፡
ደቀ መዛሙርቱ ነቢዩ ሙሴና ኤልያስን እንዳወቁአቸው ሁሉ እኛም በእግዚአብሔር መንግሥት እንተዋወቃለን፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስ “ መምህር ሆይ እዚህ መኖር ለእኛ መልካም ነው “ አለ፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስ ለሙሴ፣ ለኤልያስና ለኢየሱስ መኖሪያ የሚሆኑ ሦስት ዳሶች መሥራት አሰበ፡፡ ሙሴና ኤልያስ በዚህ ተራራ ላይ ከኢየሱሱ ጋር ለረጅም ጉዜ እንደሚሩ አሰበ፡፡ የጌታችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ መልክ መለወጥ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ ለመሆኑ ምልክት ነበር፡፡ እግዚአብሔር በደመና ውስጥ ሆኖ “ በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጂ ይህ ነው ÷ እርሱን ሰሚ “ በማለተ በመናገሩ ክርስቶስ የእገዚአብሔር ልጅ መሆኑ ይበልጥ ተገለጠላቸው /ማቴ 17÷5/ /ማር 1÷11/ ቅዱስ ጴጥሮስ በታቦር ተራራ የተመለከተውና የኢየሱስ ክርስቶስን የክብርና የብርሃነ መለካት መገለጥ ለዓለም አብያተ ክርስቲያናት በጻፈው መልእክቱ “ የእርሱን ግርማ አይተን እንጂ በብልሀት የተፈጠረውን ተረት ሳንከተል የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ኃይልና መምጣት አስታወቅናችሁ ከገናናው ክብር በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው የሚል ያድምፅ በመጣለት ጊዜ ከእግዚአብሔር አብ ክብርንና ምስጋናንን ተቀብሎኦልና ÷ እኛም በቅዱስ ተራራ ከእርሱ ጋር ሳለን ይህንን ድምፅ ከሰማይ ሲወርድ ሰማን፡፡ በማለት መሥክሮአል /2ጴ1÷17/ ከዚህ በኋላ ደቀ መዛሙርቱ ስለኢየሱስ ክርስቶስ ማንነት መጠራጠር አይኖርባቸውም÷ እርሱን ብቻ ሊሰሙ ይገባቸዋል ከዚህ በፊት ቀደም ብሎ ግን በተለይ ቅዱስ ጴጥሮስ ጌታችንን እና መድኃኔታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን ለመስማት ዝግጁ አልነበረም “ … ደቀ መዛሙርቱንም አይቶ ጴጥሮስን ገሰፀውና ወደ ኋላዬ ሂድ አንተ ሰይጣን የሰውን እንጂ የእግዚአብሔርን አታይምና አለው “ /ማር8÷32/ የእግዚአብሔርን ሐሳብና ፈቃድ ለማወቅ የሚፈልጉ ሁሉ ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሚለውን መስማት ይኖርባቸዋል፡፡ በታቦር ተራራ የምወደው ልጄ እርሱ ነው ተብሎ ከእግዚአብሔር አብ የተላለፈው መልእክት ቀደም ብሎ ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሲጠመቅ በዮርዳኖስ ወንዝም ተነግሯል፡፡ /ማቴ3÷17/ ቃና በተባለ ከተማ የሠርግ ግብዣ አድርጐ የነበረው ግለሰብ የወይን ጠጅ ባለቀበት ጊዜ የኢየሱስ ክርስቶስ እናት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የሠርገኞቹን ችግር ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንደሚአቃልልላቸው እርግጠኛ ስለነበረች አገልጋዮቹን ኢየሱስ የሚላችሁን ሁሉ አድርጐ አለቻቸው /ዮሐ 2÷5/ እርሱን ስሙ የሚለውን ቃል ሰፋ አድርገን ከተመለከትን ታዘዙት የሚል ትርጉምን ይጨምራል÷ እውነተኛው መስማት እግዚአብሔር ሲናገር ትእዛዙን ሰምቶ መታዘዝ ነው፡፡ ሐዋርያው ያዕቆብ ለእግዚአብሔር መታዘዝ አንደሚገባን ሲገልፅ “ ቃሉን የምታደርጉ ሁኑ እንጂ ራሳችሁን እያሳታችሁ የምትሰሙ ብቻ አትሁኑ ፡፡ ቃሉን የሚሰማ የማያደርገውም ቢኖር የተፈጥሮ ፊቱን በመስታወት የሚአይን ሰው ይመስላል፤ ራሱ አይቶ ይሄዳልና ÷ ወዲያውም እንደምን እንደሆነ ይረሳል፡፡
ነገር ግን ፍጹሙን ሕግ ተመልክቶ የሚፀናበት÷ሥራንም የሚሠራ እንጂ ስምቶ የሚረሳ ያልሆነው በሥራው የተባረከ ይሆናል” /ያዕ 1÷22-25/ በቁጥር 19ላይ ያዕቆብ ሰው ሁሉ ለማስማት የፈጠነ ይሁን ይላል፡፡ የእግዚአብሔርን ቃለ መስማት ብቻ በቂ አይደለም÷ መታዘዝም ያስፈልጋል፡፡ የዘለዓለም ሕይወትን የምናገኘው ቃሉን በመስማት ሳይሆን በማድረግ ነው÷ ብዙ ጊዜ ሰዎች የእግዚአብሔርን ቃል ሰምተው “ እንዴት የሚአስደንቅ ቃል ነው “ ይላሉ÷ የእገዚአብሔርን ቃል የሚአነቡና የሚወዱ ቢሆኑም ካልታዘዙት ምንም አያደርግላቸውም፡፡
እንዲውም በቃሉ ይፈረድባቸዋል፡፡ የእግዚአብሔርን ቃል የማይትዘዙ ሰዎች እውነተኛ እምነት የላቸውም÷ ራሳቸውንም ያታልላሉ፡፡ በሐዋርያው ያዕቆብ መልእክት የእግዚአብሔር ቃል እንደ መስታወት በምሳሌ ቀርቧል፡፡ ራሳችንን በመስታወት ስንመለከት እውተኛውን ፊታችንን፣እውነተኛውን ማንነታችንን፣ እናየለን፡፡ ቃሉን የምንሰማ ብቻ ከሆንን ራሱን በመስታወት ተመልክቶ፣ኃጢአቱንም አይቶ ወዲያው እንደሚረሳ ሰው እንሆናለን÷ ይልቁኑ መስታወቱ የሚአሳየንን በእርጋታ ተመለክተን ማድረግ የሚገባንን እናድርግ÷ ፊታችንን ልናጠራ፣በመስታወቱ ውስጥ ያየነውን ኃጢአታችንን ልናስወግድ ይገባናል፡፡
በዚህ ቦታ ሐወርያው ያዕቆብ ራሱን በመስታወት በሚገባ ስለሚመለከት ማለትም ፍጹሙ ሕግ የክርስቶስ ቃል የክርስቶስ ወንጌል ነው ÷ወንጌል እግዚአብሔር ሰዎችን የሚአድንበት ኃይል ነው /ሮሜ 1÷16/ ስለዚህ የክርስቶስ ወንጌል የሆነው ይህ ፍጹም ሕግ ፍጻሜው ሞት ከሆነው ከኃጢአት ቅጣት ነፃ ያወጣናለ፡፡
{flike}{plusone}