ሰበር ዜና

                                                                                                         በመ/ር ሣህሉ አድማሱ

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ከቀረጥ ክፍያ ነጻ የሆኑ አራት ዘመናዊ አዳዲስ ሞዴል መኪኖችን ገዝቶ ያስገባ መሆኑ ተገለፀ!!

0450

የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ሀገረ ስብከት የሆነው የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በ2008 ዓ.ም በያዘው መሪ ዕቅድ መሠረት ከግብርና ቀረጥ ክፍያ ነፃ የሆኑ አራት ዘመናዊ አዳዲስ ሞዴል መኪኖችን ለመግዛት ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ በወቅቱ  ለብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ ባቀረቡት ማሳሰቢያ መሠረት ከብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽ/ቤት ለፌደራል ጉዳዮች ሚኒስትር በቀረበው ማሳሰቢያ መሠረት እንደ አውሮፓውያን ዘመን አቆጣጠር የ2015 ዓ/ም ሞዴል የሆኑ አንድ V8 ላንድ ክሮዘር ፣ አንድ GX.R ላንድ ክሮዘር ፣ አንድ Toyota Hilux ፣ አንድ land curosor Prado በድምሩ አራት ዘመናዊ አዳዲስ ሞዴል መኪኖችን ከዱባይ ገዝቶ ያመጣ ሲሆን መኪኖቹ እሁድ ነሐሴ 3 ቀን 2007 ዓ.ም በሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ በሊቀ ማእምራን የማነ ዘመንፈስ ቅዱስ አስተባባሪነት ከሞጆ ደረቅ ወደብ ተነስተው መንበረ ፓትርያክ ግቢ መግባታቸው ተርጋግጧል፡፡
የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስትር ለኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ጽፎ ባስተላለፈው ደብዳቤ መሠረት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንፈሳዊና ማህበራዊ አገልግሎቷን በመላ አገሪቱ በማስፋፋት ፣ በሀገራዊ የልማት እንቅስቃሴዎች ዙሪያ ጉልህ ሚና ያለው ተግባር በማከናወን ላይ እንደምትገኝና በተጨማሪም ቤተ ክርስቲያንዋ ከመንግሥት ጋር በሰላምና መከባበር ፣ በልማት እና በመልካም ስነምግባር ግንባታ ጉዳዮች ላይ እየሠራች መሆንዋን በማስታወስ ተሽከርካሪዎቹ ለዚሁ ሥራ አጋዥ እንዲሆኑ ከቀረጥና ታክስ ነጻ ሆነው እንዲገቡ ሚ/መስሪያ ቤቱ መፍቀዱን አስታውቆአል፡፡

0438

የተሽከርካሪዎቹን ፕሮፎርማ (የዋጋ ማቅረቢያ) ለመሰብሰብ ከሀገረ ስብከቱ የተላኩት ልዑካን ሊቀጠበብት ኤልያስ ተጫነ እና ሊቀ ትጉሃን ታጋይ ታደለ በበኩላቸው የመኪኖቹን ቅድመ ታሪክ ለዝግጅት ክፍላችን ሲገልፁ ለመኪኖቹ መገዛት መነሻ የሆነው በአሁኑ ጊዜ በአገልግሎት ላይ የሚገኙት ሁለት መኪኖች የአገልግሎት ዘመናቸውን የአጠናቀቁ በመሆኑ የሀገረ ስብከቱ የአስተዳደር ጉባኤ ጉዳዩን በጥልቀት በመመልከት ባስተላለፈው ውሳኔ እና በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ ጥያቄ መነሻነት የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስቴር መኪኖቹ ከቀረጥ ክፍያ ነጻ እንዲገቡ የተፈቀደ በመሆኑ ሀገረ ስብከቱ ዱባይ ውስጥ የሚገኙትን አራት ካምፓኒዎች አወዳድሮ አሸናፊ ከሆነው ካምፓኒ ጋር ባደረገው ስምምነት አራቱንም መኪኖች በአንድ መቶ ሰላሳ አምስት ሺህ የአሜሪካ ዶላር መግዛት የተቻለ ሲሆን መኪኖቹ የተገዙት በኢትዮጵያ ምንዛሬ ከሦስት ሚሊዮን ብር ባልበለጠ ነው፡፡
አራቱም መኪኖች በቀረጥ ክፍያ ወይም በሀገር ውስጥ ሞይኮ ቢገዙ ኑሮ ከአስራ አምስት ሚሊዮን ያላነሰ የገንዘብ ወጪ ይደረግ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ ሀገረ ስብከቱ ባደረገው ከፍተኛ ጥረት መሠረት ከአስራ ሁለት ሚሊዮን ያላነሰ ገንዘብ ከማውጣት ተቆጥቦአል፡፡
በሌላ አገላለጽ አሁን ባለው ተጨባጭ የመኪና ዋጋ ሀገረ ስብከቱ በአንዱ የመኪና ዋጋ አራት መኪኖችን መግዛት የቻለ መሆኑን ያሳያል፡፡
በመሆኑም ሀገረ ስብከቱ የቤተ ክርስቲያኒቱን ሀብት በአግባቡ መጠቀም በመቻሉ በእጅጉ ሊመሰገን ይገባዋል፡፡

{flike}{plusone}