ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ የደብረ ሊባኖስ ገዳም ያስገነባውን ሁለገብ ሕንጻ ባርከው ከፈቱ!
ገዳሙ ያስገነባውን ሁለገብ ሕንጻ ቅዱስ ባርከው ሲከፍቱ
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ሐሙስ ሐምሌ 16 ቀን 2007 ዓ.ም 22 እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ተገኝተው የደብረ ሊባኖስ አንድት ገዳም ያስገነባውን ሁለገብ ሕንጻ ባርከው ከፍተዋል፡፡
ቅዱስነታቸው ሕንጻውን በባረኩበት ወቅት ሕንጻው ለገዳሙ የሚሰጠው ጠቀሜታ የጎላ መሆኑንና ሌሎቹም እንዲህ አይነቱን የልማት ተግባር ሊቀጥሉ እንደሚገባ ሰፋ ያለ አባታዊ መመሪያ አስተላልፈዋል፡፡
የገዳሙ ዋና አስተዳደሪ ፀባቴ አባ ወልደማርያም አድማሱ ባቀረቡት የሥራ ክንውን ሪፖርት ቀደም ሲል አቶ ቀፀላ እየተባሉ ይጠሩ የነበሩ አንድ በጎ አድራጊ ግለሰብ (መነኩሴ) የግል ይዞታቸው የሆነውን ባለ270 ካሬ ሜትር ቦታ ለገዳሙ በስጦታ ያበረከቱ በመሆናቸው ከ850 በላይ መነኮሳትን ለሚያስተዳድረው ገዳም የገቢ ምንጭ ይሆን ዘንድ ከ3 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ የገንዘብ ወጪ የተገነባ ሲሆን የሕንጻ ከፍታውም ባለ 4 ፎቅ ነው፡፡
{flike}{plusone}