በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የ2007 ዓ.ም በጀት መዝጊያ ኦዲት ለሚያደርጉ የሒሳብ ባለሙያዎች የሥራ መመሪያ (Orientation) ተሰጠ
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ባሉ አድባራት፣ ገዳማትና ካቴድራሎች የ2007 ዓ.ም በጀት ለሚደረገው ዓመታዊ የሒሳብ ምርመራ ሥራ ከመንበረ ፓትርያርክ ጽ/ቤት፣ ከአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤትና ከክፍለ ከተማ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ተውጣጥተው ለመጡ የሒሳብ ሙያተኞች ሰኔ 29 ቀን 2007 ዓ.ም በሀገረ ስብከቱ የመሰብቢያ አዳራሽ የሒሳብ ምርመራውን አስመልክቶ ሰፊ ገለጻ ተሰጥቷል፡፡
የሀገረ ስብከቱ ቀጥጥር አገልግሎት ዋና ክፍል ኃላፊ ሊ/ት ገብረ መስቀል ድራር ለኦዲት ሥራ የተመረጡት ባለሙያዎች የመጡበትን መሥሪያ ቤትና የባለሙዎቹን ብዛት ለተሰብሳቢዎቹ ገለጻ ድርገዋል
በዚህ መሠረት ከጠቅላይ ቤተክህነት 16፣ ከአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት 18 እና ከክፍለ ከተማ ቤተክህነት ጽ/ቤት 18 በድምሩ 52 ሲሆኑ በተጨማሪም የተመረጡበትን መሥፈርት ሲያበራሩ ባለሙያዎቹ በአካውንቲንግና በሒሳብ አያያዝ ችሎታ ያላቸው እና እስካሁን በሀገረ ስብከቱ በየዓመቱ ለሚደረገው የኦዲት ስራ ላይ ባሳዩት ታማኝነትና መልካም ስነ ምግባር ግምገማ ተደርጎ መሆኑን አያይዘው ገልጸዋል፡፡
ሊ/ት ገብረ መስቀል ከዚህ በመቀጠል አሁን በሀገረ ስብከቱ ያለው መልካም አስተዳደር ለሥራችሁ መቃናት ከፍተኛ ሚና ይኖረዋል ብለዋል’
ምክንያቱም ቀደም ሲል የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የቤተክርሰቲያኒቱን ንብረት ከብክነት ለመጠበቅና አላስፈላጊ የሆኑ አሉባልታዎችንም ለመቅረፍ ሲባል በሀገረ ስብከቱ ላሉ ገዳማት፣ አድባራትና ካቴድራሎች የሙዳየ ምጽዋት ቆጠራን አስመልክቶ መመሪያ ማስተላለፉ ይታወቃል’
በዚህ መሠረት በሁሉም አብያተ ክርስቲያናት ሙዳዬ ምጽዋት በሚቆጠርበት ጊዜ የሀገረ ስብከቱ ተወካዮች& ቤተክርስቲያኑ ባለበት አካባቢ የሚገኘው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ባለሙያዎች& የቤተክርስቲያኑ ቄሰ ገበዝ & የስብከተ ወንጌል ኃላፊ& የሰበካ ጉባኤ ተወካይ እና የሰንበት ት/ቤት ተወካይ በተገኙበት የሙዳይ ምጽዋት ቆጠራ መደረግ እንዳለበት የሚገልጽ ደብዳቤ ለሁሉም አብያተ ክርስቲያናት በመላኩ ለሥራችሁ መቃናት የበኩሉን አስተዋጽኦ ያበረክታል፡፡
ሀገረ ስብከቱ በሥራችሁ ላይ ምንም አይነት ችግር ቢፈጠር አስቸኳይ መፍትሔ በመስጠት ሁል ጊዜም ከጎናችሁ መሆኑንም ለመግለጽ እወዳለሁ፡፡
በመጨረሻም ይህን እናንተ ሠርታችሁ የምታመጡት የሒሳብ ውጤት በሀገረ ስብከቱ ሚዲያ ለሕዝበ ክርስቲያኑ ግልጽ ያደርጋል፡፡
በመቀጠልም የሀገረ ስብከቱ ቁጥጥር አገልግሎት ዋና ክፍል ኃላፊ የሒሳብ ሥራውን አስመልክተው ለባለ ሙያዎቹ ገለጻ ሲያደርጉ አጽንኦት ሰጥተው ሲናገሩ የነበረው
-ቅድመ ምርመራ
-ጊዜ ምርመራ እና
-ድህረ ምርመራ ጥንቃቄ መደረግ እንዳለበት ነው ፡፡
ቅድመ ምርመራ፡- የሚመረመሩ ሰነዶች ያሉበትን ቢሮ በአካል ተገኝቶ ማሸግና የምርመራውን ሥራ በፍጥነት መጀመር ሲሆን፤
ጊዜ ምርመራ ወይም ሒሳቡ በሚመረመርበት ወቅት ደግሞ ምንም አይነት የሥነ ምግባር ጉድለት እንዳይኖር እና ግልጽ በሆነ ሁኔታ መሥራት ፤
ድህረ ምርመራ ማለትም ከምርመራ በኋላ ሒሳቡን ያስመረመረው ክፍልና ኃላፊነት ተሰጥቷቸው ከሀገረ ስብከቱ የተላኩ የሒሳብ ባለሙያዎች የተፈራረሙበት ሪፖርት ቢዘገይ እስከ ነሐሴ 30/2007 ዓ.ም ለሀገረ ስብከቱ ማቅረብ እዳለባቸው አፅንዖት ሰጥተው ተናግረዋል፡፡
በመጨረሻ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ገዳማት አድባራትና ካቴድራሎች ከዛሬ ሐምሌ 1/2007 ዓም ጀምሮ የሚደረገውን የሒሳብ ምርመራ ሥራ በተመለከተ የዝግጅት ክፍላችን በየጊዜው እየተከታተለ ለሕዝበ ክርስቲያኑ መረጃ የሚያቀርብ መሆኑን ለመግለጽ እንወዳለን፡፡
{flike}{plusone}