የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ገዳማትና አድባራት ካህናት አዲስ ለተመደቡት ዋና ሥራ አስኪያጅና ምክትል ሥራ አስኪያጅ አቀባበል አደረጉ!!!

0010

በመናገሻ  ገነተ ጽጌ  ቅ/ጊዮርጊስ ቤ/ክ  በዋና ጸሐፊነት ሲያገለግሉ የነበሩት ሊቀ ማእምራን የማነ ብርሃን ዘመንፈሰ ቅዱስ ዋና ሥራ አስኪያጅ እና  በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤ/ክ  የሊቃውንት ጉባኤ አባል በመሆን ሲያገለግሉ የቆዩት መጋቤ ብሉይ  አእመረ አሸብር  ምክትል ሥራ አስኪያጅ በመሆን በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ተመድበዋል፡፡
 አዲስ የተመደቡት ዋና ሥራ አስኪያጅና ምክትል ሥራ አስኪያጁ  ዛሬ መጋቢት 16/2007 ዓ.ም  ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሲደረሱ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና የክፍል ኃላፊዎች እና በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሥር የሚገኙ የገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች፤  ካህናትና ሰባኪያን ወንጌል ደማቅ አቀባበል አድርገዉላቸዋል፡፡ 
በተለይ ሊቀ ማዕምራን  የማነ በዋና ጸሐፊነት ሲይገለግሉ የነበሩበት  የመናገሻ ገነተ ጸጌ  ቅ/ጊዮርጊስ ቤ/ክ ካህናት  ልብሰ  ተክህኖ በመልበስ ነበር በሀገረ ስብከቱ  አዳራሽ በመገኘት አቀባበል ያደረጉላቸው፡፡
በመቀጠልም አዲሱ ሥራ አስኪያጅና ምክትል ሥራ አስኪያጁ በሀገረ ስብከቱ አዳራሽ በመገኝት ለሀገረ ሰብከቱ ሠራተኞችና  ከየአጠቢያው ለተሰበሰቡት  የገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች፤ ሰባኪያን ወንጌልና ልዩ ልዩ ሠራተኞች አጠር ያለ ንግግር አርገዋል፡፡

0008

ተሰብሳቢዎቹም ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት በቤተክርስቲያናችን ውስጥ በላቸው የሥራ ልምድና የትምህርት ዝግጅት በግንባር ቀደምትነት ከሚታወቁት የቤተ ክርስቲያኒቱ ልጆች መካከል ሊቀ ማዕምራን የማነ ዘመንፈስ ቅዱስ እና መጋቢ ብሉይ አእመረ አሸብርን ዋና ሥራ አስኪያጅና ምክትል ሥራ አስኪያጅ  አድርገው በመመደባቸው የተሰማቸውን ደስታ ከመግለጻቸውም ባሻገር ሊቀ ማእምራን የማነ ብርሃን እና መጋቤ ብሉይ አእመረም  ያላቸውን የሥራ ልምድና የአካዳሚክ እውቀት በመጠቀም በሀገረ ስብከቱ ብሎም በሀገረ ስብከቱ ሥር ባሉ ገዳማትና አድባራት አዎንታዊ ለውጥ ማምጣት ይችላሉ ሲሉ አስተያየታቸዉን ሰጥተዋል፡፡
በመጨረሻም  ሁለቱም (ዋና ሥራ አስኪያጅና ምክትል ሥራ አስኪያጁ) በሀገረ ስብከቱ እና  በሀገረ ስብከቱ ሥር ባሉ ገዳማትና አድባራት በርካታ የተማረ የሰው ኃይል ስላለ ከነሱ ጋር በመመካከር  ለቤተክርስቲያናችን ብሎም ለሀገራችን እድገት በታማኝነት እና በቅንነት ለማገልገል  ቃል  እንገባለን  ሲሉ በሀገረ ስበከቱ ሠራተኞችና ከየአጥቢያው በተሰበሰቡት የገዳማትና የአድባራት አስተዳዳሪዎች ፊት ቃል ገብተው የዕለቱ ፕሮግራም በጸሎት ተዘግቷል፡፡    

{flike}{plusone}