የየካ ክፍለ ከተማ ቤተ ክህነት የዘመኑን ፐርሰንት ክፍያ ላጠናቀቁ አድባራትና ገዳማት ሽልማት ሰጠ

0131

በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የየካ ክፍለ ከተማ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት የ2006 ዓ.ም የበጀት ዓመት የፐርሰንት ክፍያ እስከ በጀት ዓመቱ መጨረሻ ድረስ ሙሉ በሙሉ በመክፈል መንፈሳዊ ኃላፊነታቸውን በተገቢው መንገድ የተወጡ አድባራትና ገዳማት ከክፍለ ከተማው ቤተ ክህነት የተዘጋጀ ሽልማት የሀገረ ስብከቱ ዋና ስራ አስከያጅ ሊቀ አእላፍ ቀሲስ በላይ መኮንን ፣የሀገረ ስብከቱ ምክትል ስራ አስከያጅ መምህር ኃይለማርያም አብርሃ እና የሀገረ ስብከቱ የዋና ክፍል ኃላፊዎች በተገኙበት ሽልማቱ የተሰጠ ሲሆን የሽልማቱ ተሳታፊዎች የሆኑት አድባራት እና ገዳማት፡- ሲ.ኤም.ሲ ደብረ ጽባህ ቅዱስ ሚካኤል፣አንቆርጫ ደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል፣አንቀጸ ምህረት ቅዱስ ሚካኤል፣ሲ.ኤም.ሲ መካና ጻድቃን አቡነ ተክለሃይማኖት፣ኮተቤ ሀገረ ገነት ቅዱስ ጊዮርጊስ፣ቀበና ቤዛዊተ ዓለም ቅድስት ኪዳነ ምህረት፣አያት ደብረ በረከት ቅድስት ማርያም፣ደብረ ዕንቁ ልደታ ለማርያም አብያተ ክርስቲያናት መሆናቸው ተረጋግጧል፡፡

በመጨረሻም የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ምክትል ሥራ አስኪጅ እና የአስተዳደር ዋና ክፍል ኃላፊ የፐርሰንቱ ክፍያ ተጠናክሮ ይቀጥል ዘንድ አስፈላጊውን መመሪያ አስተላልፈዋል፡፡

{flike}{plusone}