የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ፣ ያስተማራቸውን ደቀመዛሙርት በሰርተፍኬት፣ በዲፕሎማ፣ በድግሪ እና በማስተርስ አስመረቀ
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ቅዳሜ ሰኔ 28 ቀን 2006 ዓ.ም ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት፣ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ ጥሪ የተደረገላቸው ዕንግዶች እና የተመራቂ ደቀመዛሙርት ቤተሰቦች በተገኙበት ተመራቂ ደቀመዛሙርትን በሰርተፍኬት፣ በዲፕሎማ፣ በድግሪና በማስተርስ ያስመረቀ ሲሆን በርቀት መርሐ ግብር በሰርተፍኬት 83፣ በድፕሎማ መርሐ ግብር 116 በድግሪ መርሐ ግብር 78 በማስተርስ መርሐ ግብር 25 በግዕዝ ቋንቋ በዲፕሎማ መርሐ ግብር 7 በድምሩ 309 ተማሪዎችን አስመርቋል፡፡
ኮሌጁ የቀን መደበኛ እና የማታ ተከታታይ መርሐ ግብር በማውጣት የማስተማር ተግባሩን እያከናወነ የሚገኝ ሲሆን የማታውን ፕሮግራም የከፈተበት ዐቢይ ምክንያት በመንፈሳዊ አገልግሎት ዘርፍ የሴቶችን ተሳትፎ ለማበረታታት ነው፡፡
ኮሌጁን ወደ ዩኒቨርሲቲ ደረጃ ለማሸጋገር ጥረት እየተደረገ መሆኑን ብፁዕ አቡነ ጢሞቴዎስ የኮሌጁ የበላይ ኃላፊ አስታውቋል፡፡
ኮሌጁ ከማስተማር ተግባሩ ጎን ለጎን ከዚህ ቀደም ካስገነባቸው ሕንጻዎች በተጨማሪ ለቤተክርስቲያን የገቢ ምንጭ ሊሆኑ የሚችሉ ሕንጻዎችን በመገንባት ላይ ይገኛል፡፡
ይሁን እንጂ በኮሌጁ የተለያዩ ችገሮች እየተከሰቱ መሆኑን የኮሌጁ የበላይ ኃላፊ ብፁዕ አቡነ ጢሞቴዎስ አብራርተዋል፡፡
{flike}{plusone}