ለአዲስ አበባ አድባራት እና ገዳማት ተወካዮች የሥራ አመራር መግለጫ ተሰጣቸው

d0813

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘንበረ ተክለሃይማኖት በተገኙበት ሰኔ 3 ቀን 2006 ዓ.ም በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሥር ለሚገኙ አድባራት እና ገዳማት ተወካዮች በአሠሪና ሠራተኛ መካከል ስላለው ግንኙነት፣ በተመለከተ ሰኔ 3 ቀን 2006 ዓ.ም በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የስብከተ ወንጌል አዳራሽ በሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ በሊቀ አእላፍ ቀሲስ በላይ መኮንን ሰፋ ያለ መግለጫ ተሰጥቶአል፡፡
ሥራ አስኪያጁ ባስተላለፉት ሰፊ የሆነ የሥራ መመሪያ መግለጫ በአሁኑ ሰዓት የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሠራተኞች ቅጥር ሙሉ በሙሉ አቁመናል፡፡ የቅጥሩ ሁኔታ ይቀጥል ቢባልም በሚገባ ከተጠና እና አስፈላጊነቱ ከታመነበት የሠራተኛን ቅጥር ሊፈጽም የሚችለው እና ሥልጣን የተሰጠው ሀገረ ስብከቱ ብቻ ነው፡፡ የቅጥሩም አቅጣጫ ሙያን እና ቅንነትን የተከተለ ይሆናል፡፡ ቀደም ሲል በልዩ ልዩ የሥራ ዘርፍ ተቀጥረው ሲአገለግሉ የቆዩ ሠራተኞች እድገትን በተመለከተ ሕጉ በሚፈቅደው መሠረት በመጀመሪያ ከአጥቢየው በመልካም ሥነ ምግባር የተመሰከረላቸው ሠራተኞች አንደየአስፈላጊነቱ ዕድገት ሊአገኙ ይችላሉ እንጂ በግለሰቦች የእድገት ይገባኛል ጥያቄ ብቻ የዕድገት ሂደት ሊፈጸም አይገባም፡፡
በሌላ መንገድ ከአንዱ ደብር ወይም ገዳም ወደ ሌላው ደብር ወይም ገዳም ዝውውር ሊፈጸም የሚገባው ምንአልባት ችግሩ የጐላ ከሆነ ለሰላም ሲባል በተመሳሳይ ደረጃ ዝውውሩ ሊፈጸም ከሚችል በስተቀር እገሌ ይዛወርልኝ በሚል ጥያቄ ዝውውር ሊፈጸም አይችልም፡፡
ሥራ አስኪያጁ በመግለጫቸው ላይ እንደአተቱት አብዛኛውን ጊዜ የሁከት ተግባር የሚፈጽሙት በመንፈሳዊም ሆነ በሥጋዊ ዕውቀት አቅመ ደካማ የሆኑ ሰዎች ናቸው፡፡ በንግግራቸው ትኩረት ከሰጡባቸው ነጥቦች መካከል ካህናት የክህነት አገልግሎታቸውን ችላ በማለት ወደ ቢሮ ተዛውረን የጽ/ቤት ሠራተኛ እንሁን የሚል ጥያቄ በየወቅቱ ለሀገረ ስብከቱ መቅረቡ ነው፡፡ ይህ ድርጊት ሥራ አስኪያጁን በእጅጉ ያስያዝናቸው መሆኑን በአጽንኦት ገልፀዋል፡፡
በተለይም ካህናት ዋና አላማቸው ክህነታዊ አገልግሎት ሆኖ እያለ ከቆሙለት አላማ ውጭ ማሰብ ተገቢ አይደለም፡፡

d0814

ምክንያቱም ካህናት የእግዚአብሔር መንግሥት ሠራተኞች እንጂ የፋብሪካ ወይም የድርጅት ሠራተኞች አይደሉምና፡፡ በአሁኑ ጊዜ የቤተ ክርስቲያናችንን ሰላም እያናጋ ያለው በውሸት የሚናፈሱት እና መሠረት የሌላቸው የፈጠራ ወሬዎች ናቸው፡፡ እንዲህ አይነቱን የሀሰት ወሬ የሚነዙትን እና የሚያናፍሱትን ሀይሎች ሁሉም ተግቶ ሊጠብቃቸው እና ሊቆጣጠራቸው ይገባል በማለት ሰፋ ያለ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
በመጨረሻም ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ በርዕሰ አድባራት ወገዳማት አክሱም ፅዮን እየተገነባ ያለውን ታሪካዊ ሙዚየም ለፍጻሜ ለማድረስ ሁሉም የበኩሉን አደራ ሊወጣ ይገባል፣ በኢትዮጵያ መንግሥት እና ሕዝብ የጋራ ትብብር እየተገነባ የሚገኘውን የህዳሴውን ግድብ በተመለተም ሁሉም የቤተክርስቲያን ሠራተኛ የወር ደመወዙን ሊለግስ ይገባዋል፣ ሁሉም ነገር የሚከናወነው አስተማማኝ ሰላም ሲኖር ስለሆነ ሁሉም ለሰላም ዘብ እንዲቆም፣ ሙስናም እና ብልሹ አሠራርን እንዲታገል በማለት ቅዱስነታቸው አባታዊ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡

{flike}{plusone}