በአ/ሀ/ስ/የአራዳ ጉለሌ ክ/ከተማ ቤተክህነት ጽ/ቤት በወረዳው ስለ ተሠሩ ሥራዎች ሪፖርት አቀረበ

                             ሪፖርት

b003

– ብፁዕ አባታችን አቡነ እስጢፋኖስ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ረዳት እና የጅማ ሀገረ ስብከተ ሊቀ ጳጳስ

– ክቡር ንቡረ ዕድ አባ ዮሐንስ ገ/ሕይወት የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ተጠባባቂ ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ – ክቡራን የሀገረ ስብከቱ የየመምሪያ ኃላፊዎች እና ሠራተኞች

– ክቡራን የአድባራት እና ገዳማት አስተዳዳሪዎች እና የልዩ ልዩ የሥራ ኃላፊዎች

ቸሩ አምላካችን እና አባታችን ሕይወታችንን በቸርነቱ ጠብቆ፣ ሥራችንን ባርኮ እና ቀድሶ ለዚህች ሰዓት ስለአደረሰን ክብርና ምስጋና ለስመ አጠራሩ ይሁንልን አሜን::

ማዕረሩ ብዙህ በገባሩኒ ህዳጥ ሰአልዎ እንከ ለበዐለ ከመይወስክ ገባዕተ ለማዕረሩ (ማቴ. 9፡37) መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የመንግሥተ እግዚአብሔርን ወንጌል በሚአስፋፋበት ወቅት በየምኩራቡ በመሄድ የእግዚአብሔርን መንግሥት መልካም ዜና እያበሠረ ሕዝቡን ከበሽታ እና ከደዌ እየፈወሰ ህዝቡ እረኛ እንደሌላቸው በጎች ተጨንቀው እና ተቅበዝብዘው፣ ረዳት አጥተው ባያቸው ጊዜ ራራላቸው እና ከአጠገቡ ያሉትን ደቀ መዛሙርቱን መከሩ ብዙ ነው የመከሩ ሠራተኞች ግን ጥቂቶች ናቸው የመከሩ ባለቤት ተጨማሪ ሠራተኞችን እንዲልክ ለምኑት በማለት ጥበብ የተሞላበትን መልእክት አስተላልፏል፡፡

የሥራ ጀማሪ ራሱ እግዚአብሔር መሆኑን ወንጌላዊ ቅዱስ ዮሐንስ እንዲህ በማለት ይናገራል “አባቴ እስከ አሁን እየሠራ ነው እኔም ደግሞ እሠራለሁ” (ዮሐ. 5፡17) ዛሬም ቢሆን እግዚአብሔር ሥራውን አላቋረጠም፡፡ እኛም ደግሞ ከእርሱ ልንማር ይገባናል፡፡ (ማቴ. 11፡28) አምላካችን እግዚአብሔር ሰውን የፈጠረው ለሥራ እንደሆነ በቅዱስ መጽሐፍ አስቀድሞ ተናግሯል፡፡ እግዚአብሔር አምላክ ሰውን ወስዶ እንዲአለማት እና እየተንከባከበ እንዲጠብቃት በኤደን የአትክልት ቦታ አስቀመጠው (ዘፍ. 2፡15) ብርሃነ ዓለም ቅዱስ ጳውሎስ በበኩሉ ስለ ሥራ አስፈላጊነት ሲናገር ሊሠራ የማይወድ አይብላ በማለት ተናግሯል፡፡ (2ተሰ 3፡8) በዚህ ሕገ እግዚአብሔር መሠረት የአራዳና ጉለሌ ክፍለ ከተማ ቤተክህነት ጽ/ቤት ዕቅድ አውጥቶ ተገቢውን ሁለገብ የሥራ እንቅስቃሴ እያደረገ ይገኛል፡፡

የክፍለ ከተማ ቤተክህታችን የተመሠረተው ከሐምሌ 24 ቀን 2005 ዓ.ም ጀምሮ ሲሆን

በተዘረጋው መዋቅር መሰረት በርካታ ተግባራት ተከናውነዋል፡፡

ከእነዚህም የተወሰኑትን ከዚህ እንደሚከተለው እንመለከታለን፡፡

የሠው ኃይል አስተዳደርን በተመለከተ

– አስራ አንድ ሠራተኞችን የሥራ ሽግሽግ አድርገናል፤

– በዝውውር ምክንያት ደመወዛቸው ለተቀነሰባቸው ሠራተኞች ማስተካከያ ተደርጓል

– ሕገ-ወጥ ቅጥር እንዲቆም ተደርጓል

– የአሥራ ሁለት ሠራተኞች በፈቃደኝነት እና በበላይ አካል ትዕዛዝ ዝውውር ተደርጓል

– ለገዳማት እና አድባራት ጋር ከ20 ጊዜ ያላነሰ የስብሰባ ጥሪ ተላልፏል

– ከመመሪያ ውጭ በየመንገዱ ምንጣፍ በማንጠፍ ጉዝጓዝ በመጎዝጎዝ ሕገ ወጥ ልመና የሚያደርጉት ግለሰቦች በመቆጣጠር እንዲያቆሙ ተደርጓል

– ሃያ ስድስት ሰዎችን በፖሊስ አስይዘን በቁጥጥር ስር አውለናል፡፡ የፈቃድ ጊዜአቸው ያለቀባቸው 11 ሰዎችን ይዘናል፡፡

– ያለውክልና ሲሰሩ ያገኘናቸውን ስድስት ሰዎች ይዘን የተወሰኑትን በምህረት ለቀናል፡፡

– ያለአግባብ የታገዱ ሠራተኞች ወደ ሥራቸው እንዲመለሱ ተደርጓል፡፡

– የመንበረ ፀባኦት ቅድስት ሥላሴን ጨምሮ ካርታና ፕላን ያልተሰጣቸውን አድባራት እና ገዳማት ካርታ እንዲሰጣቸው አስፈላጊው ጥረት እየተደረገ ይገኛል፡፡

– የአንድነት ጉባዔ በየአድባራቱ እና በየገዳማቱ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ተደርጓል፡፡

– በየክብረ በዓላቱ ገቢን የሚቆጣጠሩ ሠራተኞችን በመመደብ አስፈላጊው ተግባር ተከናውኗል፡፡

በተለይም በአራዳ ጉለሌ ክ/ከተማ ቤተክህነት ጽ/ቤት በሥሩ የሚተዳደሩ አብያተ ክርስቲያናት የልማት ሥራዎችን በመስራት የገቢ ምንጭ በመፍጠር ገቢያቸውን በማሳደግ በበጀት ራሳቸውን እንዲችሉ በአብያተ ክርስቲያናት የጋራ ስምምነት ኮሚቴ ተቋቁሟል፡፡

ኮሚቴውም ይህንኑ ተግባር ለማከናወን የሚያስችል የገንዘብ ምንጭ ለማግኘት ገዳማቱ እና አድባራቱ ወርሐዊ አስተዋፅኦ እንዲኖራቸው ሲወሰን እንዲሁም ምዕመናንና በጎ አድራጊ ድርጅቶችን በማስተባበር በሕጋዊ ደረሰኝ የዕርዳታ ገንዘብ ለማሰባሰብ ይቻል ዘንድ ደንብ አውጥተን ለማፀደቅ በተሰጠው ኮሜንት መሰረት እነሆ ዛሬ ደንቡ ተስተካክሎ የቀረበ በመሆኑ አስፈላጊውን ተጨማሪ ሀሳብ ጉባኤው እንዲሰጥበት በዛሬው ዕለት ይዘን ቀርበናል፡፡

{flike}{plusone}