በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በአዲሱ መዋቅርዊ የአሠራር ለውጥ እና አደረጃጀት ላይ ውይይት ሊካሄድ ነው

640

አዲሱ የሀገረ ስብከቱ መዋቅራዊ የአሠራር ለውጥና አደረጃጀት እጅግ ከፍትኛ ልምድ ባላቸው የቤተ ክርስቲያኒቷ ልጆች ተዘጋጅቶ ለጥቅምት 2006 ዓ.ም የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዐተ ጉባኤ ቀርቦ ከታዬ በኋላ ለሀገረ ስብከቱ ያለው ጠቃሚነት እጅግ የላቀ መሆኑን ስለታመነበት የሚመለከታቸው አካላት ውውይት አድርገውበት በቋሚ ሲኖዶስ እንዲፀድቅ በተወሰነው መሠረት የመጀመሪያው ዙር ውውይት ህዳር 17 እና 18/2006 ለሀገረ ስብከቱ የዋና ክፍል ኃላፊዎች፤ የክፍል ኃላፊዎች፤ለክፍላተ ከተማው የሥራ ኃላፊዎች እና እንዲሁም ለጠቅላይ ቤተ ክህነት መምሪያና የድርጅት ኃላፊዎች ጋር ውውይቱ የሚካሄድ ሲሆን የሁለተኛ እና የሦስተኛው ዙር ውውይት ደግሞ ህዳር 27፤28፤29 እና 30 እና ታህሣሥ 4፤5፤6፤7፤11፤12፤13 እና 14/2006 ዓ.ም ይካሄዳል፡፡

ስለሆነም በዚሁ መሠረታዊ እና ወቅታዊ በሆነው የሀገረ ስብከቱ መዋቅርዊ የአሠራር ለውጥ እና አደረጃጀት ውይይት ላይ ክፍተኛ የሆነ ውጤት ይገኛል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በመሆኑም ሀገረ ስብከቱ ለሚያደርገው ሁለንተናዊ የሠራር ለውጥና እድገት በጋር ሆኖ መሥራት የቤተ ክርስቲያን ልጅነታችንን ከመቸውም በላይ የምናረጋግጥበት ወቅት በመሆኑ ሁሉም አቅሙ በሚፈቅደው መልኩ በአድነት መንፈስ ሊረባረብ ይገባል እንላለን፡፡

{flike}{plusone}