የምእመናን አገልግሎት

ምእመናን በሃይማኖት የጸኑ፣ በምግባር የቀኑ ይሆኑ ዘንድ በሞራል ሊገነቡ ይገባል፡፡ እንደዚህ ሲባል ግን  በእውነት ላይ የተመሰረተ ምስጋና፤ ሞራላቸውን ይገነባል ለማለት እንጂ ባልሰሩት ይመስገኑ ማለት አይሆንም፡፡ የማይገባ ምስጋና ስድብ ነው፡፡ የሚገባ ምስጋና ግን ትልቅ ሽልማት ነው፡፡ ስለሆነም ቅዱስ ጳውሎስ በሚገባ ተጠቅሞታል፡፡

‹‹ርቱዕ ናእኩቶ ለእግዚአብሔር በኵሉ በእንቲአክሙ አኃዊነ በከመ ይደልዎ፤ እስመ ዐብየት ሃይማኖትክሙ ወፈድፈደት ተፋቅሮትክሙ ምስለ ኵሉ ቢጽክሙ ከመንሕነኒ ንትመካሕ ብክሙ በቤተክርስቲያኑ ለእግዚአብሔር በእንተ ሃይማኖትክሙ፣ ወትዕግሥትክሙ፣ በሕማምክሙ፣ ወምንዳቤክሙ፣ ዘትትኤገሡ፡፡ ወንድሞቻችን ስለ እናንተ ዘወትር እግዚአብሔርን ልናመሰግነው ይገባል፤ እንደሚገባው ሃይማኖታችሁ ሰፍታለችና፤ ከባልንጀራችሁ ሁሉ ጋር ፍቅራችሁም በዝታለች፡፡ እኛም በእናንተ እንመካ ዘንድ በእግዚአብሔር ቤተክርስቲያን ውስጥ ስለ ሃይማኖታችሁ፣ ስለ ትዕግስታችሁ፣ ታግሳችሁ፣ በምትቀበሉት መከራ፡፡›› 2ኛ፡ተሰ፡1፡3-4፡፡

‹‹ወንድሞቻችን እኛስ ዘወትር እግዚአብሔርን ልናመሰግነው ይገባል፤ እግዚአብሔር ስለወደዳችሁ ስለ እናንተ የሕይወት ባለቤት እግዚአብሔር ይቅር ብሎ መርጦአችኋልና፤ በመንፈስ በመቀደስና በእውነተኛ ሃይማኖት፡፡›› 2ኛ፡ ተሰ፡1347፡፡

‹‹ሙኑ ተስፋነ ወፍሥሐነ ወአክሊለ ምክሕነ አኮኑ አንትሙ በቅድመ እግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ በምጽአቱ፡፡ እስመ አንትሙ ክብርነ ወፍሥሐነ፡፡ አለኝታችን ማነው? ደስታችንስ? የመመኪያችን ዘውድስ እናንተ አደደላችሁምን? በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ፊት በሚመጣበት ጊዜ፣ ክብራችን ደስታችን እናንተ ናችሁና፡፡››
1ኛ፡ተሰ፡2፡19-20፡፡ ወዘተ… ሲሆኑ ይህን መነሻ በማድረግ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት አገልግሎትን በተመለከተ ለሁሉም ገዳማትና አድባራት በሕጉና በደንቡ እንዲያገለግሉ መመሪያ በማስተላለፍ የአድባራትና ገዳማት ካህናት የአጥቢያው ምእመናን በአቅራቢያቸው ዘመኑ የሚፈቅደውን ሙሉ አገልግሎት ማግኘት እንዲችሉ ብዙ ሥራዎች ተሰርተዋል በመሰራትመ ላይ ይገኛሉ፡፡

  • ለአድባራትና ገዳማት አስተዳዳሪዎች የአቅም ግንባታ ሥልጠና በመሥጠት ማለትም ሁሉንም የቤተክርስቲያን አገልጋዮች እንደ ቃለ ዓዋዲው መመሪያ መሠረት ለተገልጋዩ ማኅበረ ሰብ/ምእመን በእኩል ዓይን በማየት ከአድልዎ ነፃ የሆነ ፍትሕ እንዲያሰፍኑ የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት በስርጸት ተገንዝበው እንዲተገብሩ በማድረግ፡፡
  • ለካህናቱም እነዲሁ በተመሳሳይ ሁኔታ የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት ተሰጥቶ እነሱም ደግሞ ለንሥሐ ልጆቻቸው ቢቻል በየ15 ቀናት ካልተቻለ በወር አንድ ጊዜ ንሥሐ ልጆቻቸው እየሰበሰቡ እንዲያስተምሯቸውና እንዲመክሯቸው መመሪያን ከመስጠት በሻገር አፈጻጸሙን እየተከታተለና እየገመገመ የአገልግሎት አሰጣጡ ሥርአት ዘመኑ በሚፈቅደው መልኩ እንዲሆንና  
  • በየአድባራቱና ገዳማቱ ከሌሎች ተመሳሳይ መመሪያ ኃላፊዎች ጋር በመተባበር የአገልግሎትሥራቸውን/ አገልግሎታቸውን በመገምገም የጎደለውን እንዲሟላ፤ የጠመመውን እንዲቃና እና ምእመናን ከእናት ቤተ ክርስቲያናቸው ማግኘት የሚገባቸውን መንፈሳዊና ማህበራዊ አገልግሎት ማግኘት እንዲችሉ ሀገረ ስብከቱ እስከ  አጥቢያ ድረስ ባሉ የቤተ ክርስቲያኒቱ አገልግሎት መስጫ ተቅዋማት ምእመናን የተሟላ አገልግሎት እንዲያገኙ በመስራት ላይ ነው፡፡