የቀድሞው የኦሮሚያ ክልላዊ ፕሮዝዳንት የክቡር አቶ ዓለማየሁ አቶምሳ የ80 ቀን መታሰቢያ በዓል ተከበረ፡፡
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት፣ ክቡር አቶ ሙክታር ከድር የኦሮሚያ ክልላዊ ፕሮዝዳንት፣ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ ሚኒስትሮች፣ የክቡር አቶ ዓለማየሁ አቶምሳ የቅርብ ዘመዶች እና ወዳጆች በተገኙበት ግንቦት 16 ቀን 2006 ዓ.ም በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል የአቶ ዓለማየሁ አቶምሳ የ80 ቀን መታሰቢያ በጸሎት ተከብሯል፡፡
ክቡር አቶ ሙክታር ከድር የኦሮሚያ ክልላዊ ፕሮዝዳንት የጸሎቱ ሥነ ሥርዓት እንደተጠናቀቀ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ለክቡር አቶ ዓለማየሁ አቶምሳ ያደረገችውን የጸሎት ሥነ ሥርዓት እና አክብሮት በማድነቅ ለቤተ ክርስቲያኒቱ በራሳቸው እና በክልሉ ሕዝብ ስም ምሥጋና አቅርበዋል፡፡ የትግል እና የሥራ አጋራቸው የሆኑት በክቡር አቶ ዓለማየሁ አቶምሳ ህልፈተ ሕይወት የተሰማቸውን ሀዘንም ገልጸዋል፡፡
በመቀጠልም ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ የጻድቅ ሰው ማታሰቢያ ለዘለዓለም ይኖራል በሚል ርዕስ አቶ ዓለማየሁ አቶምሳ በሥጋ ከመካከላችን ቢለዩንም በእግዚአብሔር ዘንድ በክብር ይኖራሉ፣ ክቡርነታቸው በዚህ ዓለም በሚኖሩበት ጊዜ ሀገራቸውን፣ ሕዝባቸውን በሚገባ አልግለዋል፡፡ ለሃይማኖታቸውም ታላቅ ክብር በመስጠት፣ የሚጠበቅባቸውን ሃይማኖታዊ ግዴታ በተገቢው መንገድ ተወጥተዋል፡፡ ቤተ ክርስቲያናችንም በጸሎት ስታስባቸው ቆይታለች፡፡ አቶ ዓለማየሁ አቶምሳ ለሀገር ብልፅግና ተግተው የሠሩ በመሆናቸው ሥራቸው ምሥክር ሆኖአል በማለት ቅዱስነታቸው ሰፋ ያለ አባታዊ መልእክት ካስተላለፉ በኋላ በአቶ ዓለማየሁ አቶምሳ ስም የተሠራውን ሐውልት ባርከዋል፡፡
{flike}{plusone}