በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የኢየሩሳሌም ድርጅት የ50ኛ ዓመት የወርቅ ኢዮቤልዩ በዓሉን በታላቅ ድምቀት አከበረ

00023

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት የቀድሞው የኢፊድሪ ፕሮዝዳንት ዶ/ር ግርማ ወ/ጊዮርጊስ፣ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ ጥሪ የተደረገላቸው የክብር እንግዶች እና የማኀበሩ አባላት በተገኙበት ግንቦት 16 ቀን 2006 ዓ.ም ቦሌ በሚገኘው የማህበሩ ማዕከል የ50ኛ ዓመት የወርቅ ኢዮበልዩ የምሥረታ በዓል በታላቅ ድምቀት ተከብሯል፡፡
የድርጅቱን የ50 ዓመት ጉዞ በተመለከተ በድርጅቱ የቦርድ ሰብሳቢ በአቶ ዓለምአየሁ ተስፋዬ ሰፋ ያለ ሪፖርት ቀርቧል፡፡ በታዕካ ነገሥት በዓታ ለማርያም ገዳም ሊቃውንት ያሬዳዊ ዝማሪዎች ቀርበዋል፡፡ በመጨረሻም ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ ድርጅቱ መጠነ ሰፊ ሥራ ሲአከናውን የቆየ በመሆኑ ሊመሰገን ይገባዋል፤ ቅዱስ ሲኖዶስም አስፈላጊውን ድጋፍ ሊአደርግለት ይገባል፡፡ በማለት የማበረታቻ መልእክት አስተላልፈው የድርጅቱን የሥራ እንቅስቃሴ ወደ ተሻለ ደረጃ ላደረሱት ግለሰቦች ሽልማት ሰጥተዋል፡፡

{flike}{plusone}