32ኛው የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ በመካሄድ ላይ ነው፡፡
32ኛው የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ መደበኛ ስብሰባ ጥቅምት 4 ቀን 2006 ዓም. በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ስብከተ ወንጌል አዳራሽ ተጀምሯል፡፡
በመደበኛ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤው ላይ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት፤ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፤ የመምሪያ ሓላፊዎች፤ የየሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጆች፤ ሰንበት ት/ቤት ወጣቶችና የስብከተ ወንጌል ተወካዮች፣ የአዲስ አበባ ሀ/ስብከት 160 ገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎችና የሰበካ ጉባኤ ምክትል ሊቃነ መናብርትና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡
በመጀመሪያው ቀን ውሎም የመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም ካህናት ጸሎተ ወንጌል በማድረስ የተጀመረ ሲሆን ቅዱስ ፓትርያርኩ የጉባኤውን መክፈቻ ቃለ በረከት አስተላልፈዋል፡፡
ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ የወላይታ ኮንታ እና ዳውሮ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የ2005 ዓ.ም. የሥራ ክንውን አጠቃላይ ሪፖርት በማቅረብ ጉባኤው ቀጥሏል፡፡ ብፁዕነታቸው ባቀረቡት ሪፖርት መሠረት ውይይት ተካሂዷል፡፡
እያንዳንዱ ሀገረ ስብከትም በተያዘለት መርሐ ግብር መሠረት ሪፖርቱን አቅርቧል፡፡ የ32ኛው የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ በ3ተኛው ቀን ውሎውም የየሀገረ ስብከት ሪፖርት ሲያደምጥ ውሏል፡፡ 32ኛው የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ መደበኛ ስብሰባ ጥቅምት 11 ቀን 2005 ዓ.ም. ይጠናቀቃል ፡፡
{flike}{plusone}