የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ ሊቀ ማእምራን የማነ ዘመንፈስ ቅዱስ የ2007 ዓ.ም. የትንሣኤ በዓልን አስመልክተው መልእክት አስተላለፉ

00030
ሊ/ማ/ የማነ ዘመንፈስ ቅዱስ የአ/ አ/ ሀ/ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ፡፡
እንኳን ለ2007 ዓ.ም የጌታችን፤የአምላካችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የትንሣኤው መታሰቢያ በዓል ሁላችንንም ጠብቆ አደረሰን አደረሳችሁ በማለት በራሴና በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ስም መልካም ምኞቴን እገልፃለሁ፡፡
የጌታችን ትንሣኤ የሰው ልጆች ሁሉ ከሞት ወደ ሕይወት የተሸጋገሩበት በመሆኑ የሁሉም የሰው ልጅች ትንሣኤ ነው፡፡ ክርስቶስ ሞትን ለማሸነፍ የሙታን ትንሣኤ በኩር ነው(ጀማሪ)ነው፡፡ክርስቶስ ትንሣኤ የሕይወት ትንሣኤ ነው፡፡የክርስቲያኖች  ትንሣኤ ከሞት በኋላ ብቻ የሚመጣ ትንሣኤ ሳይሆን በሕይወተ ሥጋም የሠላምና የነፃነት ምኞት የተሳካበት ትንሣኤ ነው፡፡
በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ደረጃ በዓሉን ስናከብር መልካም አስተዳደር እንዲሰፍን ፤የሥነ-ምግባር ብልሹነት እንዲወገድ ፤ቤተ ክርስቲያንን ለማገልግል ብቻ ዓላማቸው አድርገው የተማሩ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን በእኩልነትና በፍትሃዊነት እንዲስተናገዱ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት የሰጡንን አባታዊ መመሪያ ለመተግበር እንዲሁም በክርስቶስ ደም የተዋጀች ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን የሚገባትን አገልግሎት ታገኝ ዘንድ ተገቢ ማሻሻያዎችን ለማድረግ ቃል በመግባት ነው፡፡ መልካም የትንሣኤ በዓል እንዲሆንልን በድጋሚ መልካም ምኞቴን እገልፃለሁ፡፡
ሊቀ ማእምራን የማነ ዘመንፈ ስቅዱስ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ

{flike}{plusone}