የጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት በዓለ ንግሥ በደብረ አሚን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ገዳም ተከበረ!!

 

የጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት የልደታቸው ዓመታዊመታሰቢያ በዓለ ንግሥ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በመርካቶ ደብረ አሚን ተክለ ሃይማኖት ገዳም ብፁዕ አቡነ ሄኖክ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል የበላይ ጠባቂ በተገኙበት ተከበረ።
ብፁዕነታቸው በዓሉን በተመለከተ ትምህርተ ወንጌል የሰጡ ሲሆን ጻድቁንበሕይወት ልንመሥላቸው ይገባል ሲሉ አሳስበዋል።
በተጨማሪም ገዳሙ በዳግማዊ አጼ ምኒልክ ዘመነ መንግሥት በ1898 ዓ.ም የተመሠረተና 117 ዓመታትን ያስቆጠረ መሆኑን አንሥተው አሁን እየተደረገለት ላለው ሁለገብ ዕድሳት ሕዝበ ክርስቲያን በአቅማቸው ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።
በበዓሉ ላይ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከትና የክፍላተ ከተማዎች የሥራ ኃላፊዎች እንዲሁም ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ምእመናንና ምእመናን ተገኝተዋል።
©ተ.ሚ.ማ