የደቡብ አፍሪካ ሀገረ ስብከት ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ ሊቀ ጳጳስ ለነበራቸው አባታዊ ፍቅርና የእረኝነት አገልግሎት ምስጋናውን ገለጸ

የደቡብ አፍሪካ ሀገረ ስብከት ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ ሊቀ ጳጳስ ለሰጡት አባታዊ አገልግሎት ምስጋናውን ገለጸ።
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በደቡብና ምዕራብ አፍሪካ ሀገረ ስብከት ለብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ የአዲስ አበባ ሀዲያና ስልጤ አኅጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በደቡብ አፍሪካ ጁሃንስበርግ መንበረ ጵጵስና መድኃኔዓለም ካቴድራል ደማቅ አሸኛኘት መርሐ ግብር ተደረገላቸው።
በመርሐ ግብሩ ላይም ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ የአዲስ አበባ የሀዲያ ስልጤ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ ሊቀ ማእምራን መርጌታ ብርሐኑ ተክለያሬድ የደቡብና ምዕራብ አፍሪካ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ ፣የሀገረ ስብከቱ የሥራ ሐላፊዎች ፣ የአድባራት አስተዳዳሪዎች፣ ዋና ጸሐፊዎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በመርሐግብሩ ላይ ተገኝተዋል።
በመጨረሻም ብፁዕነታቸው አባታዊ መመሪያ አስተላልፈው በቃለ ምዕዳን እና ጸሎት የመርሓ ግብሩ ፍጻሜ ሆኗል፡፡
እንደሚታወቀዉ ብፁዕነታቸው በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዐተ ጉባዔ ውሳኔ መሠረት ለአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የተመደቡት መሆናቸው ይታወሳል።
© ጆሓንስበርግ ጽርሐ ጽዮን መድኃኔዓለምካቴድራል መንበረ ጵጵስና