የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ቤተ ክህነት የራሱን ቢሮ ለመገንባት የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ እንደተረከበ ተገለጸ
የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ቤተ ክህነት የራሱን ቢሮ ለመገንባት የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ እንደተረከበ ተገለጸ ።
በሥሩ ፴፭ አብያተ ክርስቲያናት ያሉት የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት የቤተ ክርስቲያን አደራ በመጠበቅ ዘመኑን የዋጀ አሠራር ተገልባራዊ ለማድረግ የተለያዩ ሥራዎችን እየሠራ እንደሚገኝ ክፍለ ከተማ ቤተ ክህነቱ ገልጿል።
ከነዚህ ሥራዎች መካከል ለክፍለ ከተማ ቤተ ክህነቱ መገልገያ ቢሮ የሚሆን ራሱን የቻለ ቢሮ ለመገንባታ የቦታ ይዞታ ማረጋገጫ ካርታ ከመንግሥት መረከባቸውን እንዱ መሆኑን አስታውሰዋል።
በዛሬ ዕለት በብፁዕ አቡነ ሄኖክ ሊቀ ጳጳስ የተመራ ልኡክ ክፍለ ከተማ ቤተ ክህነቱ የተሰጠውን ቦታ ጎብኝተዋል።
ክፍለ ከተማ ቤተ ክህነቱ የተረከበው የይዞታ ካርታ ማረጋገጫ በወረዳ 09 ቤተል አካባቢ 1ሺህ 600 ካሬ ሜትር ስፋት ያለው ሲሆን ብዙ ሥራዎች እንደሚሠሩበትም ተብራርቷል።
የክፍለ ከተማው ቤተ ክህነት ሥራ አስኪያጅ ሊቀ ትጉኃን ወንድወሰን ገብረ ሥላሴ ከአካባቢው የመንግሥት መዋቅር ጋር በመተባበር እንደሚሠሩ ገልጸው ለበርካት ድጋፉም አመስግነዋል።
ብፁዕ አቡነ ሄኖክ ሊቀ ጳጳስ ክፍለ ከተማ ቤተ ክህነቱ የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ የተረከበውን ቦታ በማየታቸው መደሰታቸውን የገለጹ ሲሆን በዚህም ክፍለ ከተማ ቤተ ክህነቱ የሥራ ሐላፊዎችንና የመንግሥት አካላትን አመስግነዋል።
ሥራዎች ተግባር ተኮር መሆን ይኖርባቸዋል ያሉት ብፁዕነታቸው ክፍለ ከተማ ቤተ ክህነቱ ከብዙ ተግዳሮት ጋር ይህን ትልቅ ሥራ በማሳካቱ ለሌሎች አርአያ የሚሆን ተግባር ነው ብለዋል።
ብፁዕነታቸው አክለውም የሁሉም ክፍላተ ከተማ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ቢሯቸው ከኪራይ ወጥተው የራሳቸውን ቢሮ እንዲገነቡ የማድረጉ ተልእኮ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል።
በተያያዘ ዜና እየተገነባ የሚገኘውን የቤቴል ደብረ ኢዮር ቅዱስ ሚካኤል ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን ገብኝተዋል።
ደብሩ እያስገነባው የሚገኘውን ግዙፍ ሕንጻ ቤተ ክርክቲያን በተለያዩ መንገዶች ገንዘብ በማሰባሰብ ሕንጻውን እያሠራ እንደሚገኙ የተገጸ ሲሆን በተለይም የደብሩ ማኅበረ ካህናት ከፍተኛውን ድርሻ ይወስዳሉም ተብሏል።