የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ቤተ ክህነት ከመንግሥት የክፍለ ከተማው ሥራ አስፈጻሚና ሥራ ሓላፊዎች ጋር የትውውቅ መርሐ ግብር አከናወነ
በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ቤተ ክህነት ከመንግሥት የክፍለ ከተማው ሥራ አስፈጻሚና ሥራ ሓላፊዎች ጋር የትውውቅ መርሐ ግብር አከናወነ።
በመር ሐግብሩ ላይ የክፍለ ከተማው ሥራ አስኪያጅ ሊቀ ትጉኃን ወንድወሰን ገብረ ሥላሴ የመንግሥት የክፍለ ከተማው ዋና ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ኒዕመተላህ ከበደና ሌሎች የሥራ ሐላፊዎች ተገኝተዋል።
ሊቀ ትጉኃን ወንድወሰን ክብርት ሥራ አስፈጻሚዋ በመምጣቻውና ትውውቅ በማድረጋቸው ደስታቸውን ገልጸው በቀጣይ ሀገር በምትከብርበት ሰውኛና ቤተ ክርስቲያናዊ አገልግሎት ላይ በጋራ ተባብሮ ለመሥራት እንደሚጠቅምም ተስፋቸውን ተናግረዋል።
በክፍለ ከተማው ቤተ ክህነትና አብያተ ክርስቲያናት የሚገኙ የሥራ ሐላፊዎችም መርሐ ግብሩ በጎ ጅምርና ለቀጣይ የአብሮነት አገልግሎት ድርሻው ሰፊ መሆኑን በመግለጽ ሐሳባቸውን ሰጥተዋል።
በመንግሥት የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ኒዕመተላህ ከበደ በበኩላቸው የትውውቅ መርሐ ግብሩ በመዘጋጀቱ መደሰታቸውን ገልጸው በቀጣይ በጋራ በመሆን በትውልድና በሰላም ግንባታ ተቀራርቦ በመሥራት ማኅበራዊና ሀገራዊ ሐላፊነቶችን መወጣት ይኖርብናል ብለዋል።
አክለውም እንደ ከዚህ ቀደሙ በቀጣይ በሚከበሩ በዓላት በሰላም እንዲያልፉ በጋራ ተቀራርበው እንደሚሠሩም አስታውቀዋል።
መረጃውን ያደረሰን ኮልፌ ቀራኝዮ ክፍለ ከተማ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ነው።
©የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሚዲያ