የእግዚአብሔር ቤት ከሰው ቤት በላይ ንፁህ መሆን አለበት……. ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ
በጉራጌ ሀገረ ስብከት በሶዶ ወረዳ ቤተ ክህነት የዶባ ጥሙጋ ደብረ ገነት ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን አዲስ በተሰራው ቤተክርሴቲያን የቅዱስ ጊዮርጊስ ቅዳሴ ቤቱ የጉራጌ ሀገረ እና አዲስ አበባ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በተገኙበት ተክብሮ ውሏል። ለበዓሉ የጉራጌ ሀገረ ስብከት የሥራ ሀላፊዎች እና የክብር እንግዶች በበዓሉ ላይ ተገኝተዋል።
በዚህ ዕለት ትውልድ እና ሀገርን በሀይማኖት አንጾ ስለመገንባት ብፁዕነታቸው ትምህርት ሰጥተዋል። የአዲሱ የዶባ ጥሙጋ ደብረ ገነት ቅዱስ ጊዮርጊስ ህንጻ ምርቃትን አስመልክቶ የእግዚአብሔር ቤት ከሰው ቤት በላይ ባማረና በተዋበ ንፁህነቱን አካቶ መሰራት አለበት ብለዋል።
የሶዶ ወረዳ ቤተ ክህነት ሥራ አስኪያጅ ሊቀ ስዩማን ጠንከር ሙሉጌታ እንደነገሩን ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ የጉራጌ እና የአዲስ አበባ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አዲስ የተገነባውን ፀበል ቤት መርቀውና ዶባ ጥሙጋ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያንን ደብረ ገነት ብለው ደብረዋል።
ቤተክርስቲያኑን በልማት ኮሚቴነት ከማህበረ ካህናቱ እና ከምዕመናኑ ጋር ህብረት ፈጥረው ለፍጻሜ ላደረሱት የምስጋና እና የምስክር ወረቀት በብፁዕነታቸው ተሰጥቷቸዋል።
በጉራጌ ሀገረ ስብከት ሶዶ ወረዳ ቤተ ክህነት በዶባ ጥሙጋ ደብረ ገነት ቅዱር ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ብፁዕነታቸው ከዋዜማው ጀምሮ የተገኙ ሲሆን ከበዓሉ ጎን ለጎን በጉራጌ ሀገረ ስብከት የተሰሩ የመንፈሳዊ እና ልማታዊ ሥራዎችን ጎብኝተዋል።
ጉራጌ ሀገረ ስብከት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በርካታ የመንፈሳዊ እና ልማታዊ ሥራዎችን በመስራት አንፀባራቂ እድገት በማስገንዘብ ላይ የሚገኝ ሀገረ ስብከት ነው። በቅርቡ በደቡብ ክልል የመጀመሪያ የሆነውን የቅዱስ ዜናማርቆስ ዘምሁር መንፈሳዊ ኮሌጅ እና የመንበረ ጵጵስና ምርቃት እና ሥራ መጀመርን አስመልክቶ መዘገባችን ይታወሣል።
በተክለሃይማኖት አዳነ ጋዜጠኛ
ለተጨማሪ መረጃ የሀገረ ስብከቱ ማኅበራዊ ድረ-ገጾችን ይጎብኙ:-
- ድረ-ገጽ:- www.addisababa.eotc.org.et
- ፌስ ቡክ ገጽ:- www.facebook.com/AddisAbabaDiocese/
- ተሌ ግራም ቻናል:- t.me/AddisAbabaDiocese
- ትዊተር :-www.Twitter.com/AddisDiocese