የኢትዮጵያ ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅደስ አቡነ ማትያስ በአሜሪካ ሐዋርያዊ ጉዞ አደረጉ
ቅደስነታቸው በአሜሪካ ባደረጉት ሐዋርያዊ ጉዞ ከበርካታ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያት ጋር ውይይት አካሒደዋል ፡፡
ብፁዕ ወቅደስ አቡነ ማትያስ ቀዲማዊ ፓትርያርክ በውይይቱ ወቅት እንደተናገሩት በዓለም ላይ የፖለቲካና የሃይማኖት ልዩነት ተፈጥሮአዊ በመሆኑ በአገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ሁሉም በጋራ እንዲሠሩ ጠይቀዋል ፡፡
ቅዱስ ፓትርያርኩና ተከታዮቻቸው በአሜሪካ በተለያዩ ክፍላተ ሀገር በመዘዋወር ስለ አንድነት፣ ሰላምና ትብብር ከኢትዮጵያውያኑ ጋር ውይይት አድርገዋል ፡፡
በአንድ ወቅት በአሜሪካን ሀገር በስደት የቆዩት ቅደስ ፓትርያርኩ በኢትዮጵያ ስላለው ተጨባጭ ሁኔታ ለኢትዮጵያውያኑ የገለፁላቸው ሲሆን በኢትዮጵያ ግልፅ የሆነ የልማትና እድገት እንደሚታይም ተናግረዋል፡፡ በመሆኑም ሁለም በውጭ አገር የሚገኙ ዜጎች ልዩነታቸውን በማጥበብ በአገራቸው በሚደረገው የልማት እንቅስቃሴ ቀጥተኛ ተሳታፊዎች እንዱሆኑ ጥሪ አቅርበውላቸዋል ፡፡
የኢትዮጵያውያን የማይቀየር ባህልና ሥርዓት በውጪው ዓለማት ተስፋፍቶና ተጠናክሮ በመቀጠሉ መደሰታቸውን ቅደስ ፓትርያርኩ ተናግረዋል ፡፡
ቅደስ ፓትርያርኩ እንዳሉት ቅዱስ ሲኖዶስ በጥቅምት ወር 2006 ዓ.ም. ባስተላለፈው ውሳኔ መሠረት ሁለም የቤተ ክርስቲያኗ አባቶች ወደተለያዩ ክፍላተ ዓለም በመዘዋወር የሰላም፣ የመቻቻልና የአንድነት ትምህርት ያስተምራሉ፤ ይህ የቅደስ ፓትርያርኩ የአሜሪካ ጉዞ የዚህ ውሳኔ አካል መሆኑንም ተናግረዋል ፡፡
በአሜሪካ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያት ከቅዱስ ፓትርያርኩ ጋር ባደረጉት ውይይት በበኩላቸው እንደገለፁት ኢትዮጵያ በስፋት የልማት ጉዞ ላይ መሆኗን መገንዘባቸውንና ሁሉም የዚህ የልማት ጉዞ ተሳታፊ ለመሆን ቁርጠኛ አቋም እንዳላቸው ተናግረዋል፡፡
በአሜሪካ የአርሜንያ፣ ሶሪያ፣ ግሪክ፣ ራሺያና የሌሎች አብያተ ክርስቲያናት ተወካዮችም ለቅዱስ ፓትርያርኩ አቀባበል አድርገውላቸዋል ፤ ውይይትም አድርገዋል ፡፡
በብፁዕ ወቅደስ አቡነ ማትያስ ቀዲማዊ ፓትርያርክ የተመራው የልዑካን ቡድን በአሜሪካ ያደረገውን ሐዋርያዊ ጉብኝት አጠናቆ ህዳር 10/2006 አዱስ አበባ ገብቷል ፡፡
ምንጭ፡-eotc-patriarch.org
{flike}{plusone}