የአዲስ ኣበባ ሀገረ ስብከት በተለያዩ ምክንያቶች ከሥራ ገበታቸው ታግድው የቆዩትን ሠራተኞች ወደ መደበኛ ሥራቸው እንዲመለሱ አደረገ
በአሁኑ ወቅት ሀገረ ስብከቱ መልካም አስተዳደር ለማስፈን እያደረገው ካለው መልካም የሥራ እንቅስቃሴ መካከል አንዱ በእንዳንድ ገደማትና አድባራት ያለአግባብ የሚታገዱትና የሚባረሩትን ሠራተኞች ትክክለኛ የሆነ ውሳኔና መፍትሄ መስጠት ነው፡፡በአሁኑ ሰዓት ገዳማትና አድባራት ከአቅማቸው በላይ ሠራተኞች በመያዛቸው የተነሳ ለጊዜው ቅጥር እንዲቆም የተደረገ ሲሆን አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ግን ለሥራ መደቡ የሚያስፈልገውን መስፈርት ወጥቶለት በህጉና በሥርአቱ መሰረት ቅጥርም ሆነ እድገት መከናውን እንዳለበት የሀገረ ስብከቱ አስተዳደር አምኖበት በሂደት ላይ ይገኛል፡፡
ወደአዲስ ቅጥር ከመከሄዱ በፊት ከአሁን በፊት ተቀጥረው በሥራ ላይ የነበሩና እና በተለያዩ ምክንያቶች ከሥራ የታገዱትን አገልጋዮች ወደ ሥራ ገበታቻው እንዲመለሱና አጠቃላይ ያለውን የሰው ኃይል በአግባቡ ማወቅ ስላለበት ከሥራ ተሰናብተው የቆዩትን አገልጋዮች በመመለስ ላይ ይገኛል፡፡በያዝነው ወር ብቻ ታግደው ከቆዩ አገልጋዮች መካከል 35 ያህሉ ወደ መደበኛ ሥራቸው እንዲመለሱ የተደረገ ሲሆን በቀጣይም እንደዚሁ የታገዱ ሠራተኞችና አገልጋዮች ካሉ ሙሉ በሙሉ የመመለስና የማስተካከል ሥራ እንደሚሰራ ለማወቅ ተችሏል፡፡ {flike}{plusone}