የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ለአዲስ አባባ ከተማ አስተዳድር የገና ስጦታ አበረከተ

በአዲስ አበባ የሃይማኖቶች ተቋማት የቦርድ ሰብሳቢ እና የአዲስ አበባና የጉራጌ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በብፅዕ አቡነ መልኬ ጼዴቅ የተመራ የአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቅዋማት ጉባኤ የልደት በዓልን ምክንያት በማድረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ም/ ከንቲባ እና ከፍተኛ የሥራ አመራሮች እንኳን አደረሳቹ በማለት በከተማዋ ለተሰሩ የመልካም አስተዳደር እና የልማት ሥራዎች በርቱ በማለት የገና ስጦታ ማበርከታቸውንና የከተማ አስተዳደሩ ሥራ በጸሎት እንደሚደግፉ በገና ስጦታ መርሀ ግብሩ ላይ መናገራቸውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በፌስ ቡክ ገጻቸው ላይ ገልጸዋል።
የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ “እኛ እንኳን አደረሳችሁ ማለት ሲገባን የአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ወደ እኛ መምጣታችሁ አስደንቆናል” ብለዋል።
ለተደረገው የአብሮነት መግለጫ የእንኳን አደረሳችሁ ስጦታ ምስጋና አቅርበው፣ ከተማ አስተዳደሩ ከአዲስ አበባ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጋር በትብብር ለመሥራት እያደረገ ያለውን እንቅስቃሴ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል።

ስጦታው ከፍተኛ የከተማ አስተዳደር አመራሮችን ያካተተ መሆኑንም ከከተማዋ ፕሬስ ሴክሬተሪ ጽ/ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

ምንጭ፦ EBC እና ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በፌስ ቡክ ገጽ