የአዲስ አበባ ከተማ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ 12ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ተካሄደ።

የአዲስ አበባ ከተማ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ 12ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ተካሄደ።
በመርሐ ግብሩ ላይ ብፁዕ አቡነ ሄኖክ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት የቦርድ ሰብሳቢ የተለያዩ የሃይማኖት ተቋማት አባቶች፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዋና አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ሙዚና ከድር፣
ከፍተኛ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሥራ ሐላፊዎች፣
የተለያዩ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እና ሌሎቹም እንግዶች ተገኝተዋል።
ጉባኤው በብፁዕ አቡነ ሄኖክ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት የቦርድ ሰብሳቢ በጸሎት ተከፍቷል።
በጉባኤው ብፁዕነታቸው የእንኳን ደኅና መጣችሁ መልእክት አስተላልፈዋል። ብፁዕነታቸው እስከ አሁን ይዘን የመጣነውን የአመለካከት ልዩነት በጋራ ተመካክረን በመሥራት ለተተኪዉ ትውልድ መልካምነትን እናዉርስ በማለት መልእክት አስተላልፈዋል።
በመርሐ ግብሩ ላይ ከተቋሙ ጋር በአጋርነት ይሠሩ ለነበሩት ተቋማት እውቅና የተሰጠ ሲሆን ለሃይማኖት ተቋማትም የእውቅና ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።©eotc tv