የአዲስ አበባ አድባራትና ገዳማት ተወካዮች ለቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ሕንጻ ግንባታ አስፈላጊውን ድጋፍ መስጠት እንደሚችሉ አስታወቁ! !

ሐምሌ 29 ቀን 2007 ዓ.ም በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሁለገብ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ብፁዕ አቡነ ጢሞቴዎስ የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ የበላይ ኃላፊ ተገኝተው እየተገነባ የሚገኘውን የኮሌጁን ሕንጻ አስመልክተው በሰጡት ሐሳብ ይህ እየተገነባ የሚገኘው ሕንጻ የኮሌጁን የማስተማር አቅም ወደ ተሻለ የዩኒቨርሲቲ ደረጃ ለማሳደግ ታስቦ ሲሆን ኮሌጁ ካለፈው ዓመት ጀምሮ ለቤተ ክርስቲያናችን ሊቃውንት ቅድሚያ በመስጠት እያስተማረ ይገኛል፡፡
ይሁን እንጂ የዲቁና ክህነት ያላቸውና እምነታቸው ጠንካራ የሆኑ ዶክተሮች እና ኢንጅነሮች በውጪ ዓለም ተሰደው የሚኖሩ በመሆናቸው ወደ ሀገራቸው ተመልሰው ዕውቀታቸውን እንዲአከፍሉ ጥሪ ቢደረግላቸውም በሀገሪቱ ካለው የኑሮ ውድነት አንጻር በድህነት አንኖርም ፣ ልጆቻችንን በምን እናሳድጋለን? እያሉን በመሆናቸው ለወደፊቱ በዶክትሬት ለሚመረቁ ከፍ ያለ ደመወዝ እየከፈልናቸው እንዲያገለግሉ እናደርጋለን፡፡
ከተሰብሳቢዎች በተሰጠው ሐሳብ እረክቼአለሁ በማለት ብፁዕነታቸው መልእክት አስተላልገዋል፡፡ ሊቀ ማዕምራን የማነ ዘመንፈስ ቅዱስም ኮሌጁ በአምስት ዓመት የማስተማር ቆይታው ተማሪዎችን በተጓዳኝ ግብረ ዲቁና ማስተማር እንደሚችል በመጠቁምና ለኮሌጁ ግንባታም ዕርዳታ የሚያሰባስቡ ኮሚቴዎችን በማቋቋም ስብሰባውን አጠናቀዋል፡፡

{flike}{plusone}