የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት በትናንትናው የእሳት አደጋ ለተጎዱ ወገኖች አጋርነቱን ገለጸ።
የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት በትናንትናው የእሳት አደጋ ለተጎዱ ወገኖች አጋርነቱን ገለጸ።
የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ ሊቀ ማእምራን የማነ ዘመንፈስቅዱስ በትናንትናው ዕለት ጥቅምት ፲፩ ቀን ፳፻፲፯ ዓ/ም በአዲስ አበባ ከተማ መርካቶ ገበያ ሸማ ተራ በተባለው አካባቢ በደረሰው የእሳት አደጋ ጉዳት ለደሰባቸው ወገኖች ባስተላለፉት መልእክት በደረሰው የሃብትና ንብረት ውድመት የተሰማቸውን ሐዘን ገልጸው።
በአደጋው ጉዳት የደረሰባቸው ወገኖች እንዲፅናኑ እና የሕይወት ውጣ ውረድ አካል መሆኑን በመረዳት ከጉዳታቸው ለማገገም በተስፋ እንዲነሳሱ አደራ ብለዋል።
የሀገረ ስብከታችን ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሄኖክ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ስብሰባ ላይ ሆነው የቃጠሎውን አደጋ በመስማታቸው ለሁሉም ተጎጂዎች የማጽናኛ መልእክት ማስተላለፋቸውን ዋና ሥራ አስኪያጁ ሊቀ ማእምራን የማነ ዘመንፈስቅዱስ ገልፀዋል።
በአደጋው ተጎጂ የሆኑ ወገኖችን መልሶ ለማቋቋም በሚደረገው ጥረት ሁሉም የኅብረተሰብ ክፍል በተለይም ክርስቲያኖች በመተባበር ክርስቲያናዊ ምግባር እንዲያሳዩ ዋና ሥራ አስኪያጁ አሳስበዋል።
መንግሥትና ኅብረተሰቡ በመልሶ ማቋቋም ሥራ ለሚያደርጉት ጥረት ሀገረ ስብከቱ የበኩሉን እንደሚወጣ እናስታውቃለን ብለዋል።
መረጃውን ያደረሰን የሀገረ ስብከቱ ጽ/ቤት ነው።