የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት ለborn again mental disorder rehabilitation center ድጋፍ አደረገ

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት በሀገረ ስብከቱ ምግባረ ሰናይ ዋና ክፍል አስተባባሪነት የተሰበሰቡ የትምህርት፣ የልብስና የምግብ ማብሰያ ቁሳቁሶችን ለborn again mental disorder rehabilitation center የበጎ አድራጎት ድርጅት አስረክቧል፡፡
ድጋፉ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ ሊቀ ስዩማን አካለወልድ ተሰማ ለድርጅቱ ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ልዑል ብረሃነ አስረክበዋል
born again mental disorder rehabilitation center ሕጋዊ የበጎ አድራጎት ድርጅት ሆኖ መንገድ ላይ ወድቀው የተገኙ የአእምሮ ታማሚዎች፣ ተጥለው የተገኙት ሕጻናትን የሚያሳድግና እስኪያገግሙ የሚንከባከብ የበጎ አድራጎት ድርጅት መሆኑን በድርጅቱ ሕዝብ ግንኙነት ኃሊፊ ልዑል ብርሃነ ተገልጸዋል፡፡
የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት የምግባረ ሰናይ ዋና ክፍል ኃላፊ ድጋፉ ከዚህ መልኩ የሚቀጥል መሆኑን ገልጸዋል
የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት ባለፉት ጊዜያት ለተለያዩ የበጎ አድራጎት ድርጅቶችን ድጋፍ እያደረገና መልካም ሥራዎቻቸውን እያበረታታ መሆኑን የሚታወስ ነው፡፡