የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት ለ53 አህጉረ ስብከት የ106 ሚልዮን ብር ድጋፍ አደረገ
በብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ የሚመራው የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት ለ53 አህጉረ ስብከት የ106 ሚልዮን ብር ድጋፍ ማድረጉን አሳውቋል።
በሀገረ ስብከቱ ድጋፍ የተደረገው የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ጥቅምት 16 ቀን 2014 ዓ/ም በወሰነው ውሳኔ መሠረት መሆኑን ተገልጿል።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በጥቅምቱ የምልአተ ጉባኤ ስብሰባው ላይ በቅቱን ተከትሎ በተለያየ ምክንያት ችግር ለደረሰባቸውና የምጣኔ ሀብቱን ተጽዕኖ ላሳደረባቸው በገጠር ለሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት ድጋፍ እንደሚያስፈልጋቸው ውሳኔ ላይ መድረሱን ይታወሳል።
ይህ በመጠኑ ዳጎስ ያለ ድጋፍ ደግሞ ከአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት አንዲከፈል በመወሰን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት ለ53 አህጉረ ስብከት ድጎማ እንዲደረግ ማሳወቁን ከቅዱስ ሲኖዶስ በቁጥር 45/423/2014 በቀን 22/2/2014 ዓ/ም ወደ አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የተጻፈ ደብዳቤ ያስረዳል።
ውሳኔውን ተከትሎ 44 አህጉረ ስብከት በተወሰነላቸው ለእያንዳንዳቸው ሁለት ሁለት ሚልዮን ብር መሠረት በጠቅላላ 88 ሚልዮን ብር የወሰዱ ሲሆን ቀሪዎቹ 9 አህጉረ ስብከት ባለው የጸጥታ ችግር ምክንያት እስካሁን እንዳልወሰዱ ተገልጿል።
የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት በየጊዜው በሀገረ ስብከቱ ምግባረ ሠናይና በተለያየ መንገድ ለተቸገሩና ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች ድጋፉን እያደረገ መሆኑን የሚታወቅ ንው።
ለተጨማሪ መረጃ የሀገረ ስብከቱን ማኅበራዊ ድረ-ገጾችን ይጎብኙ፣ like እና Join በማድረግ ይቀላቀሉ፣ ለሌሎችም ሼር ያድርጉ!!!
- ድረ-ገጽ:- www.addisababa.eotc.org.et
- ፌስ ቡክ ገጽ:- www.facebook.com/AddisAbabaDiocese/
- ተሌ ግራም ቻናል:- t.me/AddisAbabaDiocese
በመ/ር ኪደ ዜናዊ