የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የ2018 ዓ/ም የጥምቀት በዓል የቅድመ ዝግጅት ሥራዎችን በተመለከተ ውይይት አደረገ
በየዓመቱ የሚከበረውን የጌታችን የመድኃኒታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን በዓለ ጥምቀት አስመልክቶ ሀገረ ስብከቱ ከሚመለከታቸው የሥራ ሐላፊዎች ጋር በቅድመ ዝግጅት ሥራዎች ላይ ውይይት አድርጓል።
በዛሬው ዕለት በሀገረ ስብከቱ አዳራሽ የተደረገው ውይይት በመልአከ ምሕረት አባ ገብረ መድኅን ንጉሤ የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ መሪነት የተከናወነ ሲሆን የሀገረ ስብከቱ ምክትል ሥራ አክኪያጅና የዋና ዋና ክፍል ሐላፊዎች ፣ የክፍለ ከተማ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጆችና የሰው ኃይል አስተዳደር ክፍል ሐላፊዎች ተገኝተዋል።
በውይይቱ በሁሉም ክፍላተ ከተማ ቤተ ክህነት የ2018 ዓ/ም የጥምቀት በዓል አከባበር ቅድመ ዝግጅት ሥራዎች ምን እንደሚስሉ ሪፖርት በዋና ሥራ አስኪያጆች ቀርቧል።
በተጨማሪም በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ስር ያሉ አብሕረተ ጥምቀት ሕጋዊ ይዞታ፣ ጽዳህና ለበዓሉ ምቹ የማድረግ ሁኔታ፣ የሰላምና ጸጥታ የቅድመ በዓል የቅንጅት ሥራዎች ፣ ከማኅበረ ካህናት ከሰንበት ትምህርት ቤት እንዲሀ ም ከየአካባቢው ወጣቾች ጋር ውይይች መደረጋቸውም በጉባኤው ተገልጿል።
በመጨረሻም የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ መልአከ ምሕረት ቆሞስ አባ ገብረ መድኅን ንጉሤ በዓሉን አስመልክተው የሥራ መመሪያና የክትትል አቅጣጫ በመስጠት ውይይቱ ተጠናቋል።
በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ከ75 በላይ የጥምቀት በዓል ማክበሪያ ቦታዎች አብሕረት ጥምቀት የሚገኙ ሲሆን ከነዚም አንዳንዶቹ ሕጋዊ ይዞታ ስለሌላቸው ጥያቄ እየቀረበባቸው እንደሚገኙ መረጃዎች ያመለክታሉ።
