የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የገና በዓልን አስመልክቶ ለስለእናት የበጎ አድራጎት ድርጅት ድጋፍ አደረገ

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት በሀገረ ስብከቱ ምግባረ ሰናይ አስተባባሪነት የተሰበሰበ የምግብ፣የልብስ፣ የጤናና የትምህርት ቁሳቁሶችን ለስለእናት የበጎ አድራጎት ድርጅት አስረክቧል፡፡
ድጋፉ ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ የአዲስ አበባና የጉራጌ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳሰ ለስለ አናት የበጎ አድራጎት ድርጅት ፕሮግራም ኃላፊ ሙሉ ጌታ በቀለ አስረክበዋል፡፡ ብፁዕነታቸው አንድ ቀን ድርጅቱን እንደሚጎበኙ ገልጸዋል፡፡
ስለአናት የበጎ አድራጎት ድርጅት ከፍተኛ የአእምሮ የአካል ጉዳት ያለባቸውና ተጥለው የተገኙት ሕጻናትን በዘላቂነት የሚያሳድግና የሚንከባከብ የበጎ አድራጎት ድርጅት መሆኑን በ ድርጅቱ ፕሮግራም ኃሊፊ ሙሉ ጌታ በቀለ ተገልጸዋል፡፡
መ/ር ኪደ ዜናዊ የሀገረ ስብከቱ ዘጋቢ
ፎቶ በመ/ር ዋሲሁን ተሾመ